Logo
Getu Temesgen
የእንጦጦ ኪዳነምሕረት ታሪካዊ ስኬት
በሁለት ቀናት 170 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ
#ethiopia | ​ከመጋቢት 11 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በእንጦጦ ኪዳነምሕረት አዳራሽ ሲከናወን የነበረው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር፣ የገዳሟን የልማት ሥራዎች የሚደግፍ 170 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ በታላቅ ድል ተጠናቋል።

​ በአጠቃላይ 170 ሚሊዮን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 139 ሚሊዮን ብሩ በጥሬ ገንዘብ የተረጋገጠ ነው። ቀሪው 31 ሚሊዮን ብር ደግሞ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ገቢ እንደሚደረግ ቃል ተገብቷል።

​ በዝግጅቱ ላይ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ እና የገዳሟ ዋና አበመኔት መልአከ አሚን ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ይርሳው ተገኝተው መርሃ-ግብሩን መርተዋል።

​ታዋቂ ቲክታከሮች፣ ዩቱበሮች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች በዶክመንተሪና በቀጥታ ሥርጭት መርሃ-ግብሩን በማስተዋወቅ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖና የምስክር ወረቀት በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

​የ"ሎዛ ኹነቶች" ልዩ እውቅና፦ መርሃ-ግብሩን ለአንድ ወር በነጻ ሲያስተባብርና ሲያማክር የቆየው ሎዛ ኹነቶች (Loza Events) ላሳየው ላቅ ያለ አገልግሎት የወርቅ ካባ፣ የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖና የምስክር ወረቀት ከብፁዕነታቸው እጅ ተቀብሏል።

​በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ምዕመናን ለሦስት ተከታታይ ሌሊቶች በንቃት በመሳተፍ ለገዳሟ የልማት ሥራዎች መሳካት የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

​#getu #ethiopia #entotokidanemihret #orthodox #churchdevelopment #fundraisingsuccess #lozaevents #abunemekarios #spirituallegacy #የእንጦጦኪዳነምሕረት #የገቢማሰባሰቢያ #ልማት #ኦርቶዶክስ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.