Logo
SeledaPost
የኢራን ጦር ቃል አቀባይ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከስራ ተባረዋል ሲሉ ማፌዛቸዉ ተሰማ

የኢራን የካታም አል አንቢያ ማእከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋጋሪ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የሆርሙዝ ባህርን ሙሉ በሙሉ ለመክፈት የያዙት ቀነ ገደብን ተከትሎ በትራምፕ ላይ የሚያፌዝ አዲስ መግለጫ አውጥተዋል።

"ሰላም ትራምፕ ከስራ ተባረዋል፤ ለዚህ ጉዳይ ስላሳዩት ትኩረት እናመሰግናለን "በማለት ዞልፋጋሪ በእንግሊዝኛ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ተሳልቀዋል፡፡ ኢራን የሆርሙዝ የባህር ዳርቻ መዝጋቷን ተከትሎ የሀገሪቱን የኢነርጂ መሰረተ ልማት እንደምትመታ ዩናይትድ ስቴትስ የዛተች ሲሆን ይህ ከሆነ የአጸፋ ጥቃትን ለመስጠት እንደምትንቀሳቀስ ቴህራን ተደምጣለች፡፡

በሌላ በኩል የኢራን አብዮታዊ ዘብ የካታም አል-አንቢያ ዋና መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ሠራዊቱ በሳውዲ አረቢያ የሚገኘውን የልዑል ሱልጣን አየር ማረፊያ እና በባህሬን የሚገኘውን የዩናይትድ ስቴትስ አምስተኛ ባህር ኃይልን በሚሳኤል እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማጥቃቱን ተናግረዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ አውሮፕላኖች በልዑል ሱልጣን አየር ጣቢያ ላይ እንደሚገኙ ገልፆ፣ በኋላም በባለስቲክ ሚሳኤሎች ኢላማ የተደረገ መሆኑን አስታዉቋል፡፡ ለአሜሪካ ወታደራዊ ስምሪት እና ስራዎች ቁልፍ ቦታ እንደሆነም ገልጿል። በጉዳዩ ላይ ኢራን ካወጣችዉ የተናጥል መግለጫ ዉጪ ከዩናይትድ ስቴትስ ሆነ ከእስራኤል ባለስልጣናት ምንም ዓይነት የተሰጠ አስተያየት የለም።

seledadotio
seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.