Logo
YenetaTube
🚨 "ኦፕሬሽን ዕውር ቁጣ" (Operation Blind Fury) — የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደርና የዓለም ስጋት!

ታዋቂው The Economist መጽሔት በዛሬው መጋቢት 21-27 ቀን 2026 እትሙ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ዐይናቸውን በወታደራዊ ጥይቶችና ባርኔጣ በተሸፈነ ምስል በማውጣት "Operation Blind Fury" በሚል ርዕስ አስነብቧል።

መጽሔቱ አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙትን የፕሬዝዳንት ትራምፕን አስተዳደር አርቆ የማያይና በቁጣ ላይ የተመሰረተ (Blind Fury) ሲል ክርር ባለ ቋንቋ ተችቶታል።

ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው የጀመሩት "የበቀል" የሚመስል የፖለቲካ እርምጃ እና የውስጥ ተቋማትን የመቆጣጠር አካሄድ ለዲሞክራሲ ስጋት መሆኑ ገልጿል።

አሜሪካ ከቆዩ አጋሮቿ (በተለይም ከአውሮፓና ከኔቶ) ጋር ያላት ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ መሻከሩና ትራምፕ "ብቻዬን እቆማለሁ" የሚለው መመሪያቸው ዓለምን ለትርምስ ሊዳርግ እንደሚችል ተንብዮአል።

ቻይና የፊውዥን ኃይልን (Fusion Power) ለመቆጣጠር በምታደርገው ከፍተኛ ሩጫ እና በትራምፕ አስተዳደር የንግድ ጦርነት መካከል ያለው ፍጥጫ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ጠቅሷል።

መጽሔቱ በትራምፕ አስተዳደር ስር ያሉ ኢኮኖሚስቶች ለተወሰኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ያላቸውን የተዛባ አመለካከትም ነቅፏል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሁን እየተከተሉት ያለው ጠንካራና "ያልተገመተ" (Unpredictable) አካሄድ ለዓለም ሰላም ይበጃል ወይስ ስጋት ነው? የእናንተ አስተያየት ምንድነው?

👇 ሐሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን። #yenetamedia #theeconomist #donaldtrump #operationblindfury #globalpolitics #ethiopia #የኔታ_ሚዲያ

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.