Logo
Getu Temesgen
መሪር ሐዘን በኢትዮጵያ ሲኒማ
የ"አሸንጌ" ፊልም ዳይሬክተር ጳውሎስ ረጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | ​የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ አንዱን ድንቅ ባለሙያውን አጥቷል።

በፊልም ዳይሬክተርነቱ፣ በሙዚቃ ቀማሪነቱና በፖስት ፕሮዳክሽን (Post-production) ሊቅነቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ረጋሳ ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

​ጳውሎስ በተለይ "አሸንጌ" የተሰኘውን ድንቅ ፊልም ለታዳሚ በማቅረብ የሚታወስ ባለሙያ ነው።

​ለብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሲኒማ ጥበብ መምህር፣ በተግሳጽና በምክር ያሳደገ ታላቅ ወንድም እንዲሁም ነገሩ ሁሉ ፊት ለፊት የሆነ እውነተኛ ባለሙያ ነበር።

​ከዳይሬክተርነት ባለፈ በሙዚቃ ቅንብርና በፊልም ቴክኒክ ሥራዎች ላይ የነበረው ተሰጥኦ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዕድገት ትልቅ አሻራ ጥሎ አልፏል።

​ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለመላው የኪነጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ፦
መቼ እንደሚከናወን አስከሬኑ ከሕንድ ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።

የጥበብ ሰው ጳውሎስ ረጋሳ ነፍስ ይማር!

​#getu #ethiopia #cinema #filmmaking #ashengefilm #paulosregassa #art #tribute #ኢትዮጵያ #ሲኒማ #ጳውሎስረጋሳ #አሸንጌ #ሐዘን #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.