Logo
Getu Temesgen
ትኩረታችን ካራባዎ ዋንጫ ላይ ነው፦ ሚኬል አርቴታ
#ethiopia | ​የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እሁድ በዌይምብሌ ስታዲየም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ስለሚደረገው የካራባዎ ዋንጫ ፍፃሜ በሰጠው መግለጫ፣ ሙሉ ትኩረታቸው ዋንጫው ላይ መሆኑን አስታውቋል።

መድፈኞቹ ለዚህ ታላቅ ጨዋታ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

​አርቴታ በዌይምብሌ የተሻለ ነገር እንደሚያደርጉ እርግጠኛ መሆኑን ገልጾ፣ ለጨዋታው በቀሩት ሰዓታት ጥንቃቄ የተሞላበት ዝግጅት እንደሚደረግ ተናግሯል።

የሚገርመው ነገር ሚኬል አርቴታ በዌይምብሌ ስታዲየም በአሰልጣኝነትም ሆነ በተጫዋችነት ያደረጋቸውን 12ቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ አስደናቂ ታሪክ ያለው መሆኑ ነው።

​የተጫዋቾች ጤንነትና የግብ ጠባቂው ምርጫ
​በአርሰናል በኩል አዲስ የጉዳት ዜና እንደሌለ የገለጸው አርቴታ፣ የካፒቴን ማርቲን ኦዴጋርድ እና የዩሪያን ቲምበር ሁኔታ ነገ በሚደረገው የመጨረሻ ልምምድ ውሳኔ እንደሚያገኝ ጠቁሟል።

ግብ ጠባቂን በተመለከተ ከዴቪድ ራያ እና ከኬፓ አሪዛባላጋ የትኛው እንደሚሰለፍ ለቀረበለት ጥያቄ ግን "በፍፃሜው ዕለት ታዩታላችሁ" በማል ምስጢራዊነቱን ጠብቋል።

​ለአራቱም ዋንጫዎች እየተፎካከረ የሚገኘው አርሰናል፣ ይህንን ዋንጫ በማንሳት የውድድር ዓመቱን ስኬት ለማብሰር በከፍተኛ ተነሳሽነት ላይ ይገኛል።

​#getu #arsenal #manchestercity #carabaocup #mikelarteta #wembley #footballnews #eflcupfinal #አርሰናል #ካራባዎዋንጫ #ሚኬልአርቴታ #ማንችስተርሲቲ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.