ኢትዮጵያውያንን ኢራቅን ጨምሮ ኦማንና እንግሊዝ መላክ ሊጀመር ነው‼️
ኢትዮጵያውያንን ወደ ውጭ አገር ለመላክ ከመንግሥታት ጋር በሚደረግ የሁለትዮሽ ስምምነት ኢራቅን ጨምሮ ወደ ኦማንና እንግሊዝ አገሮች ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ ሥራ ፈላጊ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢራቅ፣ ኦማንና እንግሊዝ ለመላክ ከአገሮቹ ጋር ስምምነት ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው ቀውስ ሲረጋጋ ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ ስምንት ወራት በአገር ወስጥ ለ2.8 ሚሊዮን፣ በውጭ አገሮች ሥራ ሥምሪት ለሠለጠኑና በከፊል ለሠለጠኑ 447 ሺሕ፣ እንዲሁም በርቀት ለ20,537 ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል፡፡
የውጭ አገር የሥራ ዕድሉ የተፈጠረው ከዚህ ቀደም በሳዑዲ ዓረቢያ፣ በኳታር፣ በጆርዳንና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እንደነበር፣ በአዳዲስ መዳረሻዎች በተለይም ጣሊያን፣ ኩዌትና ባህሬንን ጨምሮ አራት አገሮች መጨመራቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
seledadotio

3 months ago