Logo
FastMereja
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ዓለም አቀፍ እውቅና አገኙ
#fastmereja I የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ መቀመጫውን በእንግሊዝ ለንደን ካደረገው "አፍሪካ ቢዝነስ" (African Business) መጽሔት የ2026 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴት የቢዝነስ መሪዎች (African Business Women in Leadership 2026) አንዷ በመሆን እውቅና ተሰጣቸው።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የቴሌኮም እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ላስመዘገቡት የላቀ ስኬት እና ላበረከቱት አስተዋፅኦ የተሰጠ ዓለም አቀፍ እውቅና ነው።

ተቋሙ ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባለፈ ወደ ሁለንተናዊ የዲጂታል ተጠቃሚነት እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሸጋገር በማድረጋቸው ተመስግነዋል።

ኩባንያው የቀረጸውን "ቀጣይ አድማስ፦ ዲጂታል ከዚህም ባሻገር 2028" የተሰኘ ስትራቴጂ በመምራት ተቋሙን እና የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረት በማጠናከር ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የተሰጠው ይህ እውቅና ለመላው የተቋሙ ቤተሰብ ኩራት መሆኑን ገልጾ የእንኳን ደስ አሎት መልዕክቱን አስተላልፏል።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.