የኢራን ቀሽም ደሴት ለምን በጣም አስፈላጊ ሆነች?
በኢራን ደቡባዊ ክፍል በሚገኘውና ወሳኝ የባህር መስመር በሆነው በሆርሙዝ ሰርጥ ላይ የምትገኘው ቀሽም ደሴት በአሁኑ ወቅት የዓለም ፖለቲካ ማዕከል ሆናለች።
ቀደም ሲል በተፈጥሮ ውበቷ ለቱሪስቶች ትታወቅ የነበረችው ይህች ደሴት፣ አሁን ላይ የኢራን ምስጢራዊ የከርሰ-ምድር ሚሳኤል ከተማ መሸሸጊያና ወታደራዊ የጦር ሰፈር ሆናለች።
1,445 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት ይህች ደሴት የሆርሙዝ ሰርጥ መግቢያን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልታዊ ቦታ ላይ ትገኛለች።
ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ደሴቷ ለኢራን እንደ "ማትሰምጥ የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ" ታገለግላለች።
ይህ ወታደራዊ መዋቅር በኢራን አብዮታዊ ዘብ እንደሚመራ የሚታመን ሲሆን፣ በሚሳኤሎችና በወታደራዊ ቁሳቁሶች የተሞሉ ሰፋፊ ዋሻዎችና ምስጢራዊ ተቋማት በደሴቷ ስር ይገኛሉ።
እነዚህም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ፈጣን ጥቃት ለመሰንዘር የተዘጋጁ ናቸው።
የጦርነቱ ተፅዕኖ
በአሜሪካና በእስራኤል መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ፣ ቀሽም ደሴት የቀጥታ ግጭቱ አካል ሆናለች። በየካቲት መጨረሻ አሜሪካ በሰነዘረችው የአየር ድብደባ ደሴቷ ላይ የሚገኝ ወሳኝ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያ በመጎዳቱ፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ 30 መንደሮች የውሃ አቅርቦት ተቋርጧል።
ለዚህም ምላሽ ሲሰጥ የኢራኑ ጦር በባህሬን የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር መምታቱን አስታውቋል።
የአቅርቦትና የኢነርጂ ቀውስ
ኢራን ቀሽም ደሴትን በመቆጣጠር በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚደረገውን የመርከብ እንቅስቃሴ ገድባለች። በአሁኑ ወቅት ጥቂት የነዳጅና የጋዝ ጫኝ መርከቦች ብቻ፣ ያውም በልዩ ስምምነት ብቻ፣ በቦታው ማለፍ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
ታሪክና ባህል
ቀሽም ደሴት የበለጸገ ታሪክም አላት—ጥንታውያን ግሪካውያን መርከበኞች "ኦራክታ" ብለው ይጠሯት ነበር። በፈረንጆቹ 1301 ዓ.ም የሆርሙዝ ገዥዎች ዋና ከተማቸውን ወደዚህ አዛውረው ነበር። በ1621 ደግሞ ፖርቹጋሎች በደሴቷ ላይ ምሽግ ገንብተው የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ላይ በፋርስና በእንግሊዝ ጥምር ጦር ተባረዋል።
ከወታደራዊ ጠቀሜታዋ በተጨማሪ ደሴቷ በተፈጥሮ ውበቷ ልዩ ናት። በደሴቷ ላይ የሚኖሩ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች አሁን ላይ በአንድ በኩል የተፈጥሮ ውበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የጦርነት ውጥረት በነገሰበት አስገራሚ እውነታ ውስጥ ይገኛሉ።
እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ የቀሽም ደሴት አሁን ላይ እንዲሁ መልክዓ ምድራዊ ቦታ ብቻ ሳትሆን፣ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢነርጂና የወታደራዊ ፉክክር ማዕከል ሆናለች።
ምንጭ፦ አል-ጃዚራ

3 months ago