Logo
Getu Temesgen
አርሰናል ወደ ሩብ ፍጻሜ ሲያልፍ፣
ሲቲ እና ቼልሲ ተሰናብተዋል
#ethiopia | ​የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ያልተጠበቁ ውጤቶችን አስተናግደዋል።

መድፈኞቹ በለንደን ደምቀው ሲያመሹ፣ ማንችስተር ሲቲ እና ቼልሲ ግን ከአውሮፓ ኃያላን ጋር በነበራቸው ፍልሚያ ተንበርክከዋል።

​አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ባየር ሊቨርኩሰንን 2 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት 3 ለ 1 ወደ ሩብ ፍጻሜው ተሸጋግሯል።

ለንደኖቹ ድል ኤቤሬቺ ኤዜ እና ዴክለን ራይስ ግቦቹን ያስቆጠሩ ሲሆን፣ ኤዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ የመጀመሪያ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ዘንድሮ በውድድሩ ያልተሸነፈው ብቸኛ ክለብ የሆነው አርሰናል፣ በሩብ ፍጻሜው ከፖርቱጋሉ ስፖርቲንግ ሊዝበን ጋር ይገናኛል።

​በሌላ በኩል ቼልሲ በፈረንሳዩ ፒኤስጂ ክፉኛ ተቀጥቶ ከውድድሩ ወጥቷል። በስታምፎርድ ብሪጅ 3 ለ 0 የተሸነፉት ሰማያዊዎቹ፣ በድምር ውጤት 8 ለ 2 በሆነ ሰፊ ልዩነት ተሰናብተዋል። ለፒኤስጂ ካቫርስኬሊያ፣ ባርኮላ እና ማዩሉ ግቦችን አስቆጥረዋል።

ባለፈው ዓመት ሻምፒዮን የነበረው ፒኤስጂ በሩብ ፍጻሜው ከሊቨርፑል ወይም ከጋላታሳራይ አሸናፊ ጋር ይፋለማል።

​የ15 ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮኑ ሪያል ማድሪድ በኢትሃድ ስታዲየም ማንችስተር ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ በድምር ውጤት 5 ለ 1 ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል። ቪኒሺየስ ጁኒየር የማድሪድን ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር፣ ለሲቲ ኤርሊንግ ሃላንድ ብቸኛዋን ግብ አግብቷል። በርናርዶ ሲልቫ በ20ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ መውጣቱ ለሲቲ ሽንፈት ትልቅ ምክንያት ሆኗል።

ማድሪድ በሩብ ፍጻሜው ከባየር ሙኒክ ወይም ከአታላንታ አሸናፊ ጋር ይገናኛል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.