በስነምግባር ጉድለት 6 ዳኞችን ከስራ በማገድ ተጠያቂ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ
ከዳኞች ስነምግባር ጋር ተያይዞ መንግስት በሶስት ዓመት ዕቅድ ላይ በአጠቃላይ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን እንዲካሄድ በወሰነዉ መሠረት የፍርድቤቶችን የትራንስፎርሜሽን ትግበራ ዉጤታማ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት አስታውቋል ።
ይህንንም መነሻ በማድረግ እንደ ክልልም ይሁን እንደ ዞን እንዲሁም በታችኛዉ መዋቅር የተጀመሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸዉን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሳሙኤል በፍቃዱ የተለያዩ መድረኮች ተዘጋጅተው ህዝቡ እንደ ቅሬታ ያነሳቸዉን ጉዳዮች በመለየት በ6 ዳኞች ላይ እገዳ በመጣል የህዝቡን ቅሬታ መነሻ በማድረግ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
እነዚህ 6 ዳኞች ወደ ተጠያቂነት እንዲገቡ መደረጉንና አንድ ተጨማሪ ረዳት ዳኛ በፈፀመዉ የስነምግባር ጥሰት እንዲጠየቅ መደረጉ ተገልጿል ። አሁን ላይ የ6ቱ ዳኞች ጉዳይ ሂደት ላይ መሆኑንና የዲስፕሊን ክስ ቀርቦ ፣መልስ ሰጥተዉ ፣ማስረጃ እና መከላከያ ተሰምቶ ዉሳኔ እንደሚያገኙ የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል በፍቃዱ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።
በዞኑ የፍርድ አሰጣጥ ጥራትን ለማረጋገጥ እና በፍርድ ቤቶች ላይ የሚስተዋሉ የውሳኔ አሰጣጥ መስተጓጉሎች በተገቢዉ መንገድ እንዲታዩ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል ።
በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል

5 months ago