Logo
YenetaTube
ሶማሊያ እስራኤል በሶማሊላንድ የጦር ሰፈር ለመገንባት በያዘችዉ ዕቅድ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ሶማሊያ እስራኤል በሶማሊላንድ ውስጥ የጦር ሰፈር ለመገንባት ይዛለች በተባለዉ ዕቅድ ዙሪያ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

የጦር ሰፈሩ እስራኤል አሁን እያካሄደች ላለው ጦርነት አካል በመሆን በቀጣናው ባሉ ጠላቶቿ ላይ የአየር ድብደባ ለማድረግ እንደ ስልታዊ ነጥብ የሚያገለግል ይሆናል።

ሀገሪቱ ግዛቷ ‹‹በውጭ ግጭቶች›› ውስጥ እንዲገባ እንደማትፈልግ ገልጻለች።

በኤደን ባሕረ ሰላጤ ማዶ ከየመን ፊት ለፊት የሚገኘው ይህ የጦር ሰፈር፤ እስራኤል በየመን የሚገኙትን የሁቲ አማጺያን፣ እንዲሁም በኢራን እና በሊባኖስ የሚገኘውን ሄዝቦላህን ጨምሮ በሰፊው ቀጣና ውስጥ በሚገኙ ጠላቶቿ ላይ ስልታዊ የአየር ጥቃቶችን እና ድብደባዎችን እንድትሰነዝር ያስችላታል።

እስራኤል ባለፈው ታህሳስ ወር የሶማሊላንድን ነጻነት ዕውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገር ስትሆን፤ በዚህም ሂደት ከሶማሊላንድ ጋር አጋርነት መስርታለች።

የሶማሊላንድ ባለሥልጣናት በየካቲት ወር መጀመሪያ ላይ እስራኤል በግዛታቸው ላይ ወታደራዊ ሰፈርን ልትመሰርት የምትችልበትን ዕድል ውድቅ ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል።

የሶማሊላንድን እውቅና ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆነችው ሶማሊያ፤ እስካሁን ያሉትን እነዚህን ሁኔታዎች በስጋት ስትከታተል ቆይታለች።

Ethio Fm

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.