Logo
YenetaTube
የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ ልጃቸው ሥልጣኑን የመረከቡ ጉዳይ ያሳስባቸው እንደነበር የአሜሪካ የስለላ መረጃ አሳየ

የቀድሞው የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ልጃቸው እርሳቸውን ተክቶ ሥልጣን እንዲይዝ የማድረግ ሀሳብ ላይ ጥርጣሬ እንደነበራቸው የአሜሪካ የስለላ መረጃ ማሳየቱን የቢቢሲ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ዘገበ።
ይህንን የሚገልጸው የስለላ መረጃ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በዙሪያቸው ላሉ ጥቂት ሰዎች እንደቀረበ ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ያሳያል።

የቀድሞው አያቶላህ ልጃቸው ሞጅታባ ኻሜኒ ብሩህ ጭንቅላት አለው የሚባል ባለመሆኑ እንዲሁም ለመሪነት ብቁ የሆነ ሰው ተደርጎ ባለመታየቱ ሥልጣኑን እንዳይረከብ ስጋት እንደነበራቸው የአሜሪካ ስለላ ትንተና አመልክቷል ተብሏል።

በተጨማሪም አባት በልጃቸው የግል ሕይወቱ ውስጥ ስላለው ችግር ያውቁ እንደነበር መረጃው እንዳሳየ ምንጮቹ ተናግረዋል።
አያቶላህ አሊ ኻሜኒ አሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ ከሳምንት በፊት ልጃቸው ሥልጣኑን ተረክበዋል።
አዲሱ ጠቅላይ መሪ በዚህ ሳምንት የሰጡት የመጀመሪያ መግለጫ በአገሪቱ ቴሌቪዥን ቢነበብም ሥልጣኑን ከተረከቡ ወዲህ እስካሁን አልታዩም።

ሞጅታባ ሳይጎዱ አልቀሩም የሚሉ መረጃዎች ወጥተዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አግራቺ ግን ጠቅላይ መሪ “ጥሩ ጤንነት ላይ” እንደሚገኙ እና “ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ” መሆኑን በዛሬው ዕለት ተናግረዋል።

BBC

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.