Logo
FastMereja
ፍቅር ኢትዮጵያ አለም አቀፍ የዳውንሲድረምን ቀን በልዮ ልዩ ስፖርት ወድድሮች በድምቀት አከበረ ።

‎የዓለም የዳውን ሲንድሮም ቀንን ምክንያት በማድረግ “Let me win, but if I cannot win, let me be brave in the attempt" ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉ ስፖርታዊ ዉድድር በዛሬዉ እለት በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በይፋ ፍፃሜውን አግኝቷል።

‎የእለቱ የክብር እንግዳ ክብርት ሁሪያ አሊ የሴቶችና የማህበራዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ : የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሎምፒክ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ግርማ ዘውድ: የፍቅር ኢትዮጵያ ፕረዝደንት ምህረት ንጉሴ : የኢትዮጵያ ስፔሻል ኦሎምፒክ ብሄራዊ ፅህፈት ቤት ሃለፊ የሆኑት ወ/ሮ ትርስተወልድ አበባ አየሁን : ሽዋጌጥ ክብረት የፍቅር ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እና ከተለያዩ ክልሎች ተሳታፊ ስፖርተኞችና አመራሮች በተገኙበት መቋጫውን አግኝቷል።

‎በአለም ለ15ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው በዚህ ፕሮግራም ላይ የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክብርት ሁሪያ አሊ የሴቶችና የማህበራዊ ሚኒስቴር ሚኒስትር መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ስለ down syndrome በማህበረሰባችን ትልቅ ክፍተት ስላለ ይህን አመለካከት የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ይገባል የሚመለከታቸው አካላት በየደረጃው
‎በትምህርት ቤት: በሃይማኖት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ መሰራት እንዳለበት ገልፀው መንግስትም የሚጠበቅበትን ይወጣል ብለዋል

‎ከመጋቢት 4 ጀምሮ እስከ መጋቢት 6 ድርስ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የነበረው የስፖርት ወድድር
‎አዲስ አበባ በ10 ወርቅ 12 ብር 3 ነሃስ 1ኛ :
‎ድሬዳዋ በ10 ወርቅ 3 ብር 1 ነሃስ 2ኛ : አማራ በ6 ወርቅ 1 ብር 4 ነሃስ 3ኛ : ሲዳማ በ2 ወርቅ 1 ብር 2 ነሃስ 4ኛ
‎ሲይዙ በግል 2 ወርቅ 2 birr 1ነሃስ ተመዝግባል።

‎በእለቱም አርቲስት ሰሎሞን ተካ : ደራሲና ዳይሬክተራ የራስ ወርቅ ግርማ እና አርቲስት ይመር አባተ የስፔሻል ኦሎምፒክ በጎ ፍቃድ አምባሳደር በመሆንም ተመርጠዋል።


5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.