የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የሕይወት ታሪክ
ወንድም ተዋበ ወንድሙ እንዳነበበው
#ethiopia | የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን አባቶች፣ ቤተሰቦችና የመምህር ዘላለም ወዳጆች፤ ዛሬ የምንናገረው ስለ አንድ ሥጋዊ ወንድማችን ብቻ አይደለም፤ የምንናገረው ስለ ብዙዎች አባት፣ ስለ ድሆች ረዳትና ስለ ወንጌል ብርሃን ነው። መምህር ዘላለምን በሥጋ መለየታችን ለአንጀታችን እጅግ የሚከብድ፣ ለቤተሰባችንም መሪር ሐዘን ቢሆንብንም፤ እርሱ ግን አስቀድሞ በመልካም ሥራው በሰማይ ቤት ቤቱን ሰርቶ እንደነበር እናምናለን።
ምንም እንኳን በሰውነታችን ብናዝንም፣ በብጹዓን አባቶቻችን ጸሎትና ትምህርት፣ እንዲሁም በዚህ በመካከላችሁ ባላችሁትና "አለንላችሁ" በሚሉን የክርስቶስ ቤተሰቦች ፍቅር ተጽናንተናል። እርሱ የሄደው ወደ ፈጠረው አምላክ ነውና ሐዘናችን በተስፋ የተሞላ ነው።
የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የሕይወት ታሪክ
ውልደትና የልጅነት ዘመን
መምህር ዘላለም ወንድሙ (ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት) ከአባታቸው ከአቶ ወንድሙ ተማም እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ትክክልወርቅ ገብረኢየሱስ ነሐሴ 17 ቀን 1969 ዓ.ም በታሪካዊቷ ደብረ ሲና ከተማ ተወለደ። ገና በለጋነቱ የቤተክርስቲያንን ጠረን እየሳበ፣ በየኔት ታመነ እግር ሥር ተቀምጦ የቄስ ትምህርቱን በመቅሰም ለወደፊቱ መንፈሳዊ ተጋድሎው መሠረት ጣለ።
የትምህርት ጉብዝና እና የቅንነት መገለጫ
በትምህርቱ እጅግ ብሩህ የነበረው ዘላለም፣ በሰበታ ከተማ በነበረው የትምህርት ቆይታው ሁልጊዜም ከአንደኛነት አይወርድም ነበር። በተለይም በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች 100% በማምጣት አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል።
የሚገርመው ግን ዕውቀቱ ለራሱ ብቻ አልነበረም፤ ለሒሳብ ትምህርት የነበረው ልዩ ተሰጥኦ መምህራኑ በማይኖሩበት ጊዜ እርሱ መምህር ሆኖ ጓደኞቹን ያስተምር ነበር። ይህ "ሌሎችን የማብቃት" መልካም ባሕሪው ገና በልጅነቱ አብሮት ያደገ ጸጋው ነበር።
ከአግሮ ቴክኒክ ወደ ወንጌል አገልግሎት
በወሊሶ አግሮ ቴክኒካል ትምህርት ቤት በኤሌክትሪሲቲ ሙያ በዲፕሎማ ቢመረቅም፣ የልቡ ጥሪ ግን የሰው ልጅን ነፍስ በወንጌል ኤሌክትሪክ ማብራት ነበር። በወሊሶ ቆይታው ከብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እግር ሥር ሆኖ በሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎቱን ጀመረ። የ12ኛ ክፍል ውጤቱ ለከፍተኛ ኮሌጅ ቢያበቃውም፣ እርሱ ግን "የእግዚአብሔር መንግሥት ትቀድማለች" ብሎ ራሱን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት አሳልፎ ሰጠ።
የአገልግሎት አሻራዎች፡ ከከተማ እስከ ገጠር
መምህር ዘላለም "የከተማ ኑሮ ይመቸኛል" ብሎ የተቀመጠ አገልጋይ አልነበረም። እግሩ ወንጌል ባልደረሰባቸውና እርዳታ በሚሹ አካባቢዎች ሁሉ ደርሷል፦
በደቡብ ኦሞ ገጠራማ ስፍራዎች፡ ለማሌ፣ ሰሜን አሪ እና በና ፀማይ ብሔረሰቦች አምስት አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ የቃለ ወንጌል ብርሃን እንዲበራ አድርጓል። ሌላው ቀርቶ የሌላ እምነት መሪዎችን አስተምሮ በማስጠመቅ አዳራሻቸውን ወደ ቤተክርስቲያንነት እንዲቀየር አድርጓል።
ለቋንቋ ተናጋሪዎች የሰጠው ትኩረት፡ በ2003 ዓ.ም ከ38 ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተውጣጡ ደቀ መዛሙርትን አምጥቶ፣ ወጪያቸውን ሸፍኖ ካሰለጠነ በኋላ ወደየአካባቢያቸው እንዲያገለግሉ ልኮአቸዋል።
ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳማትና አድባራት አባቶች የሚሰጡትን ምስክርነት ሳያካትት ካከናወናቸው ዋና ዋና ሥራዎች፡
ደቡብ ኦሞ ገጠራማ ሥፍራዎች
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት የከተማ አገልጋይ ብቻ አልነበረም፡፡ በደቡብ ኦሞ ገጠራማ ሥፍራዎች ቃለ ወንጌልን በማስተማር ካበረከተው መንፈሳዊ አልግሎት በተጨማሪ፡
1. ለማሌ ብሔረሰብ -የማሌ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን
2. ለሰሜን አሪ ብሔረሰብ-የዘፍቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
3. ለአሪ ብሔረሰብ-የሰልማ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
4. ለበና ፀማይ ብሔረሰብ-የሙቃጫ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
5. የማላተር ቅዱስ ሚካኤል-በጅምር ላይ ያለ፡ በከተማው የነበሩትን ዋና ዋና ፓስተሮች
አስተምሮ በማስጠመቅ፣አዳራሻቸውን አፍርሰው ቆርቆሮውን በማምጣት
እንዲሠራ አድርገዋል፡፡
ጉሙዝ፣ጋምቤላ፣ጂንካ
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት በ2003 ዓ.ም ከጠረፋማዋና ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ 38 ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ደቀ መዛሙርትን መልምሎና ከየሀገረ ስብከታቸው ማስረጃ አስጽፎ በማስመጣት ሙሉ የሥልጠና ወጪያቸውን በመሸፈን በጽርሐ ጽዮን የሥልጠና ማዕከል እንዲማሩ በማድረግ ሥልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ፣ የአገልግ ሎት ልብስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ገዝቶ በመስጠት ወደየመጡበት አካባቢ ተመልሰው በቋንቋቸ ው እንዲያገለግሉ አድርጓል፡፡
ጅጅጋ
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በጅጅጋ በደረሰው ችግር የተጎዱትን ለማጽናናት በሥፍራው ጉባኤ በማዘጋጀት ማኅበረ ምእመናንን ከማጽናናቱ በተጨማሪ ሰዎችን በማስተባበር ከ1,500,000.00 (ከአንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ በማሰባሰብ በወቅቱ ለተጎዱ የሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ካህናት ድጋፍ እንዲያገኙ በመርዳት የቤተክርስቲያን ልጅነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡
ሰበታ ቅዱስ ገብርኤል
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ለ57 ዓይነ ስውራን በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ለዘለቄታው ራሳቸውን የሚችሉበት ቦታ በመግዛት እንቅስቃሴ አስጀምሯል፡፡
በምሁር ኢየሱስ ገዳም
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት 12 ልጆችን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በማስመጣት ዲቁና እንዲማሩና ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው እንዲያገለግሉ አድርጓል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ-በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ 2591 ሰዎች *3,000 ብር =7,773,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ሸዋሮቢት፣አጣዬና ከሚሴ-ከተለያዩ አካባዎች ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ አበርክቷል፡፡
ደብረ ዘይት-መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ከቢሾፍቱ ከተማ በቅርብ ከሚገኘውና የኢትዮጵያ አውሮፕላን ተከስክሶ ብዙ ሰው ባለቀበት ኤጄሬ ቦታ ላይ በአካል ተገኝቶ በማጽ ናናትና የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስን በማስፈቀድ የተለያዩ ሰዎችን በማስተባበር የቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያንን አስተክሎ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአካል በመገኘት አስመርቋል፡፡
ቡታጅራ-በግጭት የተፈናቀሉትን ቦታው ድረስ ሄዶ በአካል በመገኘት በቃለ እግዚአብሔር ከማጽናናት በተጨማሪ የሚታወቅበትን መልካምነት በድጋፍ አሳይቷል፡፡
ከስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ በክርስትናቸው ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ለ288 ሰዎች *2,000 ብር =576,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
አርሲ ሻሸመኔ ባሌ
ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉ እና ለተፈናቀሉ ክርስቲያኖች ሩዝ፣ዱቄት፣ዘይት እና የማሰያ ዕቃዎችን በማቅረብ መንፈሳዊ ኀላፊነታቸውን ተወጥቷል፡፡
አፋር
በአፋር ክልል ለሚገኙ በዞን 5 ሰሙሮቢ ወረዳ ኩማሜ አካባቢ -በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ 495 ሰዎች* 3,000 ብር =1,485,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ስሙን "ማሩ!" በማለት የሚጠሩት የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሲኖዶስ አባ ብጹዕ አቡነ ዮናስ በስማቸው በዋሽ ዐርባ ለተቋቋመው አረጋውያን የጡረታ ማእከል የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን እና በኀላፊነት በማገልገል ዓመታዊ የምግብ እገዛ አድርጓል፡፡
ደብረ ሊባኖስ ገዳም-ለአበው ካህናት ለአገልግሎት የሚሆን ልብሰ ተክህኖ ሰጥቷል
ደብረ ብርሃን-የአእምሮ ሕሙማን ማገገሚያ እንዲሆን በአርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያም ልጅ በተመሠረተው ሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ለንጽሕና መጠበቂያ የሚሆኑ ነገሮችን በማቅረብ ሃይማኖቱን በተግባር አስመስክሯል፡፡
ዋግህምራ ዞን ሰቆጣ- በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ901 ሰዎች *3,000 ብር =2,703,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ደባርቅ ወረዳ በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ294 ሰዎች *3,000 ብር =882,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ጎንደር-የአብነት ተማሪዎች ሲመረቁ ካባ ሰጥቷል፡፡
አዲስ አበባ
ይዲድያ መንፈሳዊ ማኅበር
እኁድ ከ 5፡00-7፡00 ሰዓት በቃለ እግዚአብሔር በሃይማኖት በምግባር እንዲጸኑ፣ እንዲያድጉና እንዲበረቱ ከማስተማር በተጨማሪ ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለችግር የተጋላጡ ልጆችን በማስተማር ራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ እስረኞች ለዳግም ትንሣኤ የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ይዲድያ የሕፃናት መርጃ
ይዲድያ የሕጻናት መርጃ ድርጅት በመምህር ዘላለም ወንድሙ መሥራችነትና አስባባሪነት በበጎ አድራጎት የተሰማራ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ያለ ሃይማኖት፣ያለዘር፣ያለ ቋንቋ ልዩነት ወገናዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡ በይዲድያ የሕጻናት መርጃ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ልጆች ከ2008-2018 ባሉት ለ12 ዓመታት ከ2650 በላይ ለሆኑ ልጆች ከ15,000,000.00 ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወገናዊ ደጋፉን በማድረግ ላይ የሚገኝ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት 200 ልጆችን በመርዳት ላይ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ በዝቅተኛ ኑሮ ለተቸገሩ 1000 ሰዎች 3,000 ብር =30,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
በየሳምንቱ ረቡዕና ዓርብ የሚደረግ የምሣ ምገባ
ሀ. ቂርቆስ 80 ልጆችን ፤ለ. ሣሪስ አቦ 148 ልጆችን፤ ሐ. የካ ሚካኤል 72 ልጆችን ባጠቃላይ ለ300 አቅመ ደካሞችን የምሣ የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ለሚገኙ ጸበልተኞች ዘይትና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ወንጌለ ዘላለም ከተባለው የዩቲዩብ ቻናላቸው ከሚገኘው ገቢ፡
ግቢ ገብርኤል፣የወደቁትን አንሡ፣እንጦጦ ማርያም….ለሚገኙ ዐቅመ ደካሞች በበዓለ ጰራቅሊጦስ የዘይትና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል፡፡
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ለአገልግሎት በሄዱበት በሀገረ አሜሪካ በገጠማቸው ድንገተኛ ሕመም የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ49 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፏል፡፡
የመምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕትን ነፍስ በቅንነትና በታማኝነት ያገለገሉት አምላክ በአብርሃም፣በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን፡፡ለኦርዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ለቤተሰቡ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ያድልልን፡፡
✍️ “ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤”
በወንጌል አላፍርምና፤
አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም
ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ
የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። ሮሜ 1÷14
እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን
ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
ስለ ሃይማኖት መሪዎች አባቶቻችን እንጸልይ
ስለ ሀገር መሪዎች እንጸልይ
የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን
አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም
መጋቢት 3/7/2018 ✍️

5 months ago