Logo
Getu Temesgen
ለሁሉም የሚሽከን (Mishkan) ኮሌጅ ተማሪዎች በሙሉ የቀረበ አጣዳፊ የጥንቃቄ መልዕክት

​ጉዳዩ፦ የተማሪዎች መረጃ ዝውውር እና የአገልግሎት አሰጣጥን ይመለከታል

​በቀድሞ ስሙ ሚሽከን ኮሌጅ ተብሎ የሚጠራው ተቋም፣ በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በሰጠው መመሪያ መሠረት ተማሪዎቹን ወደ ሐጌ (Hage) ኮሌጅ ማስተላለፉ ይታወቃል። ስለሆነም ተማሪዎች መረጃዎቻቸው ለባለስልጣኑ እንዲላኩና ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ የሚከተሉትን ነጥቦች በአጽንኦት እንዲገነዘቡ ይሳሰባል፦

​ዋና ዋና ነጥቦች

​የጊዜ ገደብ፦
የተማሪዎችን መረጃ ለባለስልጣኑ ለማስገባት የተሰጠው ጊዜ እጅግ አጭር (አንድ ወር ብቻ) በመሆኑ፣ ተማሪዎች በአስቸካይ ወደ ሐጌ ኮሌጅ በመምጣት አገልግሎት ማግኘት ይኖርባቸዋል።

​ከማጭበርበሪያ ድርጊቶች ተጠንቀቁ፦ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባና በክፍለ ሀገር "በሚሽከን ኮሌጅ ስም ጉዳይ እናስፈጽማለን፣ መረጃችሁን እናስጨርሳለን" በማለት ተማሪዎችን ለእንግልትና ለአላስፈላጊ ወጪ የሚዳርጉ አጭበርባሪ አካላት መኖራቸው ተደርሶበታል።

​ብቸኛው የአገልግሎት መስጫ፦ ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት የሚቻለው በሐጌ ኮሌጅ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ራሳችሁን ከአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

​አድራሻ እና ስልክ
​ቢሮ፦ ሐጌ ኮሌጅ ዋናው ቢሮ (የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12፣ ኮተቤ ካራ በሬ ተራ ፊት ለፊት፣ አያና ጋሮማ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ)።

​ስልክ፦
📞 0975737741 ወይም 0934433438 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

​ማሳሰቢያ፦ ተማሪዎች ይህንን አጭር የጊዜ ገደብ ተረድተው መረጃዎቻቸውን በአካል በመገኘት እንዲያሳርፉ በድጋሚ እናሳስባለን።

​#ሚሽከንኮሌጅ #ሐጌኮሌጅ #የትምህርትናስልጠናባለስልጣን #አጣዳፊመልዕክት #ተማሪዎች #ጥንቃቄ #ኢትዮጵያ #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.