Logo
FIDEL POST NEWS
ኢራን በካሊፎርኒያ ላይ የድሮን ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል FBI አስጠነቀቀ

​የአሜሪካው የምርመራ ተቋም (FBI) በካሊፎርኒያ የፖሊስ ጣቢያዎች ላይ አስቸኳይ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አስተላለፈ።

ኢራን በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ከሚገኙ ማንነታቸው ካልታወቁ መርከቦች በመነሳት ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች ተብሎ ተሰግቷል።

ይህ ዕቅድ ከየካቲት ጀምሮ የተጠነሰሰ ሲሆን፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ለምትወስደው ወታደራዊ እርምጃ ምላሽ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

​ከዚህ በተጨማሪ፣ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ቡድኖች በድንበር አካባቢ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ ድሮን በመጠቀም ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ የስለላ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ጥቃቱ መቼ እና የት ላይ እንደሚፈጸም ግልጽ መረጃ ባይኖርም፣ የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ FBI አሳስቧል።

​ምንጭ፦ ABC News
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.