ተያዥ ሆኖ ያስቀጠራት ግለሰብ ሰርቃ በሰጠችው ገንዘብ እና ንብረት ተሽከርካሪ የገዛው ግለሰብ በ7 ዓመት እስራት ተቀጣ፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ7 ልዩ ቦታው ቀበና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ታምሩ በቀለ የተባለው ተከሳሽ አቶ ኃይሉ ፍቅረ በተባሉት የግል ተበዳይ ቤት ውስጥ በሰራተኝነት ያስቀጠራት እህቱ ወንጀሉን መፈፀሟን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡
ለጊዜው በቁጥጥር ስር ያልዋለችውና በፖሊስ ክትትል እየተደረገባት የምትገኘው ተጠርጣሪዋ፤ የተቆለፈውን የግል ተበዳይ የመኝታ ቤታቸውን በር ሰብራ በመግባት በመኝታ ቤቱ ውስጥ ተቀምጦ የነበረ 20ሺህ ዩሮ እና 22ግራም የሚመዝኑ የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን በአጠቃላይ ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ገንዘብ እና ንብረት በመስረቅ ለወንድሟ ሰጥታ እንደተሰወረች የፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡
የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግለሰቧን ተያያዥ ሆኖ ያስቀጠራትን ታምሩ በቀለ የተባለውን ወንድሟን በቁጥጥር ስር በማዋል ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ተግባር ተሰርቆ በተሰጠው ገንዘብና ንብረት የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-20790ኦሮ ሰሌዳ የለጠፈ ዶልፊን ተሽከርካሪ ገዝቶ ሲገለገልበት እንደነበር በማረጋገጥ ተሽከርካሪው በኤግዚቢትነት እንዲያዝ ተደርጓል፡፡
ፖሊስ በተከሳሹ ላይ የምርመራ መዝገብ በማደራጀት በአቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተበት በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት የካቲት 26/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በ7 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡
በተሰረቀው ገንዘብና ንብረት የተገዛው ተሽከርካሪ በተመለከተ በፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ተሽከርካሪው ወንጀሉ ለተፈፀመባቸው የግል ተበዳይ እንዲሰጣቸው ተወስኗል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል

5 months ago