Logo
YenetaTube
ራሺያ የአሜሪካን የጦር መርከቦች ለመምታት የሚያስችል የስለላ መረጃ ለኢራን ማጋራቷ ተነገረ

ራሺያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ የጦር መርከቦችን፣ አውሮፕላኖችን እና ሌሎች ወታደራዊ ንብረቶችን ኢራን ኢላማ እንድታደርግ የሚያስችል ወሳኝ የስለላ መረጃ ማጋራቷን የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት ገለጹ።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሁለት የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት ለሚዲያ እንደተናገሩት፤ የሞስኮ ይህ እርምጃ ሩሲያ አሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ጦርነት ውስጥ በይፋ እጃቸውን እያስገቡ መሆኑን የሚያሳይ የመጀመሪያው ፍንጭ ነው ተብሏል።

እንደ ባለስልጣናቱ ገለጻ፣ ሩሲያ ያጋራችው መረጃ ኢራን በቀጠናው የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሃይሎችን በከፍተኛ ጥንቃቄ ለመምታት እንድትችል የሚረዳ ነው።

ይሁን እንጂ አሜሪካ እስካሁን ባለው መረጃ ሩሲያ መረጃውን ከመስጠት ባለፈ ኢራን ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባት ትዕዛዝ ስለመስጠቷ የደረሰችበት ማስረጃ እንደሌለ ባለስልጣናቱ አክለው ገልጸዋል።

ይህ የሩሲያ እርምጃ ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ እና በእስራኤል የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ በቀጠናው ያለውን ውጥረት ይበልጥ ሊያባብሰው እንደሚችል ተሰግቷል። እስከ አሁን በጉዳዩ ላይ ከሞስኮም ሆነ ከቴህራን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።

Ethio Fm

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.