ዶናልድ ትራምፕ የቀጣዩን የኢራን መሪ ምርጫ ላይ "እጃቸው መግባት እንዳለበት" ገለጹ
#fastmereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀጣዩን የኢራን መሪ በመምረጡ ሂደት ላይ በግል መሳተፍ እንደሚፈልጉ በዛሬው ዕለት ለኤክሲዮስ በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታወቁ።
ትራምፕ ከኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ህልፈት በኋላ፣ አዲሱን የሀገሪቱን መሪ በመሰየሙ ሂደት ላይ እሳቸው በግላቸው መሳተፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።
ትራምፕ የሟቹ መሪ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸው ተተኪ የመሆን ከፍተኛ ዕድል እንዳላቸው ለኤክሲዮስ አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ሞጅታባ ኻሜኒ የአባታቸውን ቦታ ተረክበው መሪ መሆናቸው "ተቀባይነት የሌለው" ውጤት እንደሆነም ትራምፕ በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው አስገንዝበዋል።
ይህ የትራምፕ አስተያየት አሜሪካ በቀጣይ በኢራን የውስጥ ፖለቲካ እና በመሪዎች ሽግግር ላይ ጠንከር ያለ ተጽዕኖ ለማሳደር ያላትን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

3 months ago