Logo
FastMereja
5ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት በአዲስ አበባ በይፋ ተከፈተ!
#fastmereja I ​“ራስን መቻል ለዘላቂ ሰላምና ለአካታች ልማት” በሚል መሪ ቃል፣ 5ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዛሬ በየካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በይፋ ተከፍቷል።

​ከ120 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራዎቻቸውን ለህዝብ በኤግዚቢሽን የሚያቀርቡበት ሲሆን፣ እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ጎብኚዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

ዝግጅቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።

​በቆይታው በስምንት አበይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ። ከነዚህም መካከል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና በጠቅላላ ምርጫ፣ በሰላም ግንባታ፣ በስርዓተ ጾታ እና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ይገኙበታል።

​በመድረኩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ የልማት አጋሮች እና የሚዲያ አካላት ተገኝተዋል።

​ይህ መድረክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እርስ በርስ እንዲተዋወቁና ከህዝብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።
#ኹነት

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.