የኢራቅ የኤሌክትሪክ ኃይል መረብ ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ
የኔታ ሚዲያ
በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ቀጠናዊ ግጭት በኢራቅ ላይ ከባድ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ቀውስ እያስከተለ ይገኛል የኢራቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የሀገሪቱ ብሔራዊ የኃይል መረብ (National Grid) ሙሉ በሙሉ በመደረመሱ ምክንያት በመላ ሀገሪቱ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል።
ምንም እንኳን ሚኒስቴሩ በይፋ "ምርመራ እያደረግኩ ነው" ቢልም የችግሩ መነሻዎች ኢራን የሆርሙዝ ስልጥን (Strait of Hormuz) መዝጋቷን ተከትሎ ለኢራቅ የኃይል ማመንጫዎች የሚያስፈልገው የጋዝ እና የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ተስተጓጉሏል
•lበአሜሪካ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ለአምስት ተከታታይ ቀናት የቀጠለው ከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት የኢራቅን መሠረተ ልማቶች ለከፍተኛ ጫና ዳርጓቸዋል።
ኢራቅ በቀን 1.5 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ምርቷን ለመቀነስ ተገድዳለች። ይህም የሆነው ነዳጅ የምታከማችበት ቦታ በማጣቷና በባህር በኩል ለዓለም ገበያ ማቅረብ ባለመቻሏ ሲሆን ይህም በኃይል ዘርፉ ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል።
በአሁኑ ሰዓት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢራቃውያን ያለምንም የኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኙ ሲሆን ይህም እንደ ሆስፒታሎች እና የውሃ አቅርቦት ባሉ ወሳኝ አገልግሎቶች ላይ ስጋት ፈጥሯል የኩርዲስታን ክልል (Kurdistan Region) በተወሰነ መልኩ የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት ቢኖረውም አጠቃላይ የሀገሪቱ የኃይል ስርዓት ግን በታሪኩ እጅግ አስከፊ ለሚባል ውድቀት ተጋልጧል።
የኢራቅ መንግስት የኃይል መረቡን በከፊልም ቢሆን ወደ ስራ ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ቢገልጽም የቀጠናው ውጥረት እስካልረገበ ድረስ ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት አስቸጋሪ እንደሚሆን ተገምቷል።

3 months ago