እስራኤልና ኢትዮጵያ በደህንነት ጉዳዮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የእስራኤል መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት በደህንነት ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር መስማማቱን በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ አስታወቀ።
የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ በኢትዮጵያ ካደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ጋር ተያይዞ፣ አምባሳደር አቭራሃም ንጉሴ ለአሐዱ ራድዮ እንደገለጹት፤ ፕሬዝዳንቱ ከከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በደህንነት፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም በደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
አምባሳደሩ የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት የጉብኝቱ አጀንዳ እንዳልነበረ ጠቁመው፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የእስራኤል ታማኝና ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗን አረጋግጠዋል። ይህ ታሪካዊ ግንኙነት በስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
አሑዱ ራዲዮ

3 months ago