የሰብዓዊነትና የደግነት ተግባር በህፃን ብሌን መኖሪያ ቤት
#ethiopia | ከንቲባ አዳነች አቤቤ ላለፉት 10 ዓመታት በከፍተኛ የአንጎል ውስጥ ውሃ እና የአንጎል ግፊት መጨመር (ሀይድሮሴፋለስ) ምክንያት የአልጋ ቁራኛ የሆነችውን ህፃን ብሌን አሸናፊን በመኖሪያ ቤቷ ተገኝተው ጎብኝተዋል።
፩. የህክምና ድጋፍ፦
ህፃን ብሌን ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ ለምትታከምበት የህክምና ወጪ የሚያስፈልገውን 4 ሚሊዮን ብር ከንቲባዋ ለወላጅ አባቷ አስረክበዋል።
ለዚህ በጎ ተግባር አጠቃላይ የህክምና ወጪውን በመሸፈን ለተባበሩት ክቡር ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ከንቲባዋ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
፪. የአርአያነት ተምሳሌት የሆኑት አባት፦
የብሌን አባት ወጣት አሸናፊ፣ በከተማዋ የጽዳት ሰራተኛ ሆኖ እየሰራ፤ ያለ እናት እርዳታ ብሌንን፣ ታናሽ እህቷን፣ አካል ጉዳተኛ እህቱን እና አረጋዊት እናቱን የሚንከባከብ ጠንካራና ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ወጣት ሆኖ ተገኝቷል።
፫. የመኖሪያ ቤት መፍትሄ፦
ቤተሰቡ በአሁኑ ወቅት የሚኖርበት ቤት ለህፃኗ የፊዚዮቴራፒ ህክምናም ሆነ ለጤንነቷ አመቺ ባለመሆኑ፣ አስተዳደሩ ለቤተሰቡ የተሻለ መኖሪያ ቤት እንዲያገኝ ውሳኔ አስተላልፏል።
፬. የመልካም ምኞት መግለጫ፦
ከንቲባዋ ህፃን ብሌን ከህመሟ አገግማ እንደ እኩዮቿ የምትቦርቅበትና ትምህርት የምትጀምርበት ጊዜ ቅርብ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል። በተለይም የ7 ዓመቷ ታናሽ እህቷ ማርያም አሸናፊ ብሌንን ለማጫወት የምታደርገው ጥረት ልብ የሚነካ እንደነበር ገልጸዋል።
"ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!"
— ከንቲባ አዳነች አቤቤ
#ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ከንቲባአዳነችአቤቤ #ሰብዓዊነት #በጎነት #ብሌንአሸናፊ #getu #temesgen #getutemesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

3 months ago