ከሳህ እስከ ካሜኒ ግድያ : የአሜሪካ እና ኢራን የ80 ዓመታት የጥላቻና የሴራ ታሪክ
ከኮስታስ ቡሩሲስ ፅሁፍ የተወሰደ
የአሜሪካ እና የኢራን ግንኙነት ላለፉት 80 ዓመታት በዓለም ፖለቲካ ውስጥ እጅግ አስገራሚ፣ አስፈሪ እና መርዛማ ከሚባሉ የታሪክ ምዕራፎች አንዱ ነው።
ይህ ግንኙነት በ1940ዎቹ በሳህ (Shah) ቤተ መንግሥት ውስጥ በደስታና በወዳጅነት ተጀምሮ፣ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ስጦታ ታጅቦ፣ በመጨረሻም በ2026 የአሊ ካሜኒን ግድያ ተከትሎ ወደ ተሟላ ጦርነትና ውዝግብ አምርቷል። ይህን ረጅም ጉዞ በዝርዝር እንመልከተው።
እ.ኤ.አ በ1943 ፍራንክሊን ሩዝቬልት፣ ቸርችል እና ስታሊን በቴህራን ተገናኙ። በወቅቱ ኢራን "የድል ድልድይ" ተብላ ትታወቅ ነበር። አጋሮቹ የቀድሞውን ንጉሥ አባረው ወጣቱንና ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚመቸውን መሐመድ ሬዛ ፓህላቪን በዙፋን ላይ አቆዩት። አሜሪካውያን ለወጣቱ ንጉሥ ምዕራባዊ የአኗኗር ዘይቤን በማስተዋወቅና ድጋፍ በመስጠት ኢራንን በመካከለኛው ምስራቅ ታማኝ ወኪላቸው አደረጓት።
በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ የኢራን ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሞሳዴቅ የኢራንን የነዳጅ ሀብት ወደ መንግሥት ለማዞር ወሰኑ። ይህ ውሳኔ ብሪታንያንና አሜሪካን ክፉኛ አስቆጣ።
በ1953 የሲአይኤ "ኦፕሬሽን አጃክስ" በተባለ ሴራ ሞሳዴቅን ከሥልጣን አወረደ። ንጉሡ ሳህ ወደ ሥልጣን ተመለሰ።
በ1957 አሜሪካ ለሳህ ልዩ ስጦታ አበረከተች። "Atoms for Peace" በተባለው ፕሮግራም አማካኝነት የመጀመሪያውን የኒውክሌር ሬአክተር ለቴህራን ሰጠች። ዛሬ አሜሪካን እያስጨነቀ ያለው የኢራን ኒውክሌር መሠረቱ በአሜሪካ እጅ የተጣለ መሆኑ የታሪክ ምፀት ነው።
በ1960ዎቹ ሳህ ኢራንን ወደ ምዕራባዊ ሥልጣኔ ለመቀየር "ነጭ አብዮት" አወጀ። ይሁን እንጂ ይህ ለውጥ በሃይማኖታዊ መሪዎችና በድሆች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም።
በ1970ዎቹ መጀመሪያ አሜሪካ ኢራንን "የባህረ ሰላጤው ፖሊስ" አድርጋ ሾመቻት። ፕሬዝዳንት ኒክሰን "ከኒውክሌር ውጭ የፈለገውን መሣሪያ ሽጡለት" በማለት ለኢራን ቢሊዮኖችን አፈሰሱ።
ሆኖም በኢራን ውስጥ የነበረው ሙስና እና የሳህ የደህንነት መስሪያ ቤት (SAVAK) የሚያደርሰው ግፍ ሕዝቡን አሰለቸው።
በ1979 አያቶላ ሆሜኒ ከስደት ተመልሰው እስላማዊ አብዮቱን መሩ። ሳህ አገር ጥሎ ፈረጠጠ። በዚያው ዓመት ህዳር ወር ላይ ኢራናውያን ተማሪዎች የአሜሪካን ኤምባሲ በመውረር 52 አሜሪካውያንን ለ444 ቀናት ታገቱ። ይህ ክስተት በአሜሪካና በኢራን መካከል የነበረውን ግንኙነት ለዘላቂ ጥላቻ ዳረገው። አሜሪካ "ታላቁ ሰይጣን" ተብላ ተጠራች።
በ1980ዎቹ አጋማሽ አሜሪካ ለኢራን በድብቅ መሣሪያ የሸጠችበት "ኢራን-ኮንትራ" የተባለው ቅሌት ተከሰተ። ይሁን እንጂ በ1988 የአሜሪካ የጦር መርከብ በስህተት የኢራን የመንገደኞች አውሮፕላን (Flight 655) መትቶ በመጣሉ 290 ንጹሐን ሞቱ። ይህ ቁስል እስካሁን አልሻረም።
በ2002 ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ ኢራንን ከሰሜን ኮሪያና ኢራቅ ጋር በመፈረጅ "የጥፋት ዘንግ" (Axis of Evil) ብለው ጠሯት። ይህ በቴህራን በኩል ትልቅ ክህደት ተደርጎ ተቆጠረ።
በ2015 ፕሬዝዳንት ኦባማ በዲፕሎማሲያዊ ጥረት የታሪክ ለውጥ አመጡ። የኢራን የኒውክሌር ስምምነት (JCPOA) ተፈረመ። ሆኖም በ2017 ዶናልድ ትራምፕ ሥልጣን ሲይዙ ከዚህ ስምምነት ወጥተው በኢራን ላይ "ከፍተኛ ጫና" አሳደሩ።
በ2020 የኢራኑ ጄኔራል ቃሲም ሱሌይማኒ በአሜሪካ ድሮን መገደል ሁኔታውን ወደ ጦርነት አቀረበው።
እ.ኤ.አ. የ2025 የዶናልድ ትራምፕ ዳግም መመረጥ ለኢራን አገዛዝ የመጨረሻው መጀመሪያ ነበር። በሰኔ 2025 አሜሪካና እስራኤል "Midnight Hammer" በሚባል ዘመቻ የኢራንን የኒውክሌር ማዕከላት ደበደቡ። ኢራንም በኳታር በሚገኝ የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በሚሳኤል ምላሽ ሰጠች።
በመጨረሻም በየካቲት 2026 (እ.ኤ.አ) አሜሪካና እስራኤል በወሰዱት የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አሊ ካሜኒ እና የኢራን አብዮታዊ ዘብ አመራሮች ተገደሉ። ይህ ክስተት በቴህራን ጎዳናዎች ላይ ትልቅ ውዝግብና ለውጥን ፈጥሯል።
የአሜሪካና የኢራን ግንኙነት ከወዳጅነት ወደ ደም አፋሳሽ ጠላትነት የተቀየረበት ታሪክ ለዓለም ትልቅ ትምህርት ነው። በ1943 በፈገግታ የተጀመረው ጉዞ በ2026 በሚሳኤል ድምፅ ደምድሟል።
ዛሬ ኢራን አዲስ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች፤ የመካከለኛው ምስራቅ የወደፊት ዕጣ ፈንታም ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ሆኗል።

4 months ago