አድዋ በአትላንታ 🇪🇹🇺🇸
130ኛው የድል በዓል በ"ስቶን ማውንቴን" ደመቀ
#ethiopia | በአሜሪካ አትላንታ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 130ኛውን የዓድዋ የድል በዓል "የድል እንጂ የነፃነት ቀን የለንም!" በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት አክብረዋል።
በ"ጉዞ ዓድዋ በአትላንታ ማህበር" አዘጋጅነት በስቶን ማውንቴን ፓርክ በተደረገው በዚህ ስምንተኛ ዙር የእግር ጉዞ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን በጠዋት በመሰባሰብ የጋራ ታሪካቸውን ዘክረዋል።
የትውልድ ቅብብል፦
አሜሪካ ተወልደው ያደጉ ሕፃናት የታሪኩ ባለቤት እንዲሆኑ "ለልጆች በልጆች" በሚል መርህ ታሪካቸውን እንዲማሩና እንዲደምቁበት ተደርጓል።
ታሪካዊ ስያሜዎች፦
በጉዞው ወቅት ወርኢሉ፣ አምባላጌ፣ መቀሌ እና ዓድዋ ተብለው የተሰየሙ ቦታዎች ተዘጋጅተው ታሪካቸው ለተሳታፊው ቀርቧል።
የአንድነት ድምቀት፦
ዕድሜ፣ ዘር፣ ጾታና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉም ተሳታፊ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በሚመስል "ሁዲ" (Hoodie) ደምቆ ታሪኩን በጋራ አክብሯል።
የምኒልክ የግብር አዳራሽ፦
በጉዞው ማጠናቀቂያ ላይ በ"ምኒልክ የግብር አዳራሽ" ሁሉም ተሳታፊ የማዕዱ ተቋዳሽ እንዲሆን ተደርጓል።
🙏 የምስጋና ጥሪ
ይህ ታላቅና የተሳካ ፕሮግራም እንዲካሄድ ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ለረጅም ጊዜ የደከሙ የጉዞ ዓድዋ አስተባባሪዎች ማህበሩ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።
#አድዋ130 #ጉዞዓድዋ #አትላንታ #ኢትዮጵያ #የድልበዓል #ስቶንማውንቴን #adwa130 #guzoadwa #atlanta #ethiopia #stonemountain #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago