Logo
FastMereja
"የአያቶላ አሊ ኻሜኒ ግድያ በሙስሊሞች ላይ የታወጀ የጦርነት አዋጅ ነው" የኢራን ፕሬዝዳንት

​#fastmereja I የአሜሪካ እና የእስራኤል ጥቃት የኢራንን ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒን መግደሉን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዘሽኪያን ድርጊቱን "በሙስሊሞች ላይ የታወጀ የጦርነት አዋጅ" ሲሉ ገለጹ።

​ፕሬዝዳንቱ ባወጡት መግለጫ "የኢስላማዊት ሪፐብሊክ ኢራን ከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የሺዓ መሪ መገደል፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሚገኙ ሙስሊሞች በተለይም በሺዓዎች ላይ በግልጽ የታወጀ የጦርነት አዋጅ ተደርጎ ይወሰዳል" ብለዋል።

​ኢራን የዚህ "ታሪካዊ ወንጀል" ፈፃሚዎችን እና አቀናባሪዎችን የመበቀል ሕጋዊ ግዴታ እና መብት እንዳላት ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።

ይህ ግድያ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያሸጋገረ ሲሆን፣ የኢራን መንግስት ጠንካራ ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.