Logo
YenetaTube
አሊ ሬዛ አራፊ በጊዜያዊነት ኢራንን እንዲመሩ ተመረጡ

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ መገደላቸውን ተከትሎ አሊ ሬዛ አራፊ ሀገሪቱን በጊዜያዊነት እንዲመሩ መመረጣቸውን ኢራን ኢንተርናሽናልና አል ጀዚራ ዘገቡ።

ክስተቱ የተከናወነው በኢራን መዲና ቴህራን ሲሆን፤ ጠቅላይ መሪው አያቶላህ አሊ ኻሜኒ በእስራኤልና አሜሪካ ጥቃት በቢሯቸው ውስጥ መገደላቸውን ተከትሎ ሀገሪቱ የ40 ቀን ብሔራዊ የሐዘን ቀን አውጃለች።

እንደ ዘገባው ከሆነ አዲሱ ተመራጭ አሊ ሬዛ አራፊ ከፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን እና ከፍትሕ ሚኒስትር ጎላም ሆሴይን ሞህሴኒ ኤጄይ ጋር በመሆን የሽግግር አመራር ምክር ቤት አባል ሆነው ተመርጠዋል።

አሊ ሬዛ አራፊ የተገደሉትን ጠቅላይ መሪ ቦታ ተክተው እንደሚሠሩ አል አረቢያ የዘገበ ሲሆን፤ በ1937 በማሽሀድ ተወልደው በ86 ዓመታቸው የተገደሉት አሊ ኻሜኒ መላውን ኢራን ለ35 ዓመታት በበላይነት መምራታቸው ይታወሳል።

አዲሱ የሽግግር አመራር ምክር ቤት ሀገሪቱ ያለችበትን የጦርነት ውጥረትና ቀጣዩን የጠቅላይ መሪ ምርጫ የማመቻቸት ኃላፊነት እንደሚኖርበት ተመላክቷል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.