Logo
FastMereja
ሰሜን ኮሪያ በኢራን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት "ሕገ-ወጥ ወረራ" ስትል አወገዘች

​ሰሜን ኮሪያ እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ የሰነዘሩት ጥቃት የሀገርን ሉዓላዊነት የጣሰ "ሕገ-ወጥ ወረራ" ነው ስትል መኮነኗን የሀገሪቱ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን (KCNA) ዘግቧል።

​የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እሁድ ዕለት በሰጡት መግለጫ፣ የአሜሪካ ወታደራዊ እርምጃ የሀገሪቱን "ወሮበላ" ባሕርይ የሚያሳይና የሚጠበቅ ነበር ብለዋል።

በእስራኤልና አሜሪካ የተከፈተው "የወረራ ጦርነት" በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት የለውም። የኢራን ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን ተከትሎ፣ ጥቃቱ በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ አለመረጋጋት ይፈጥራል የሚል ስጋት ነግሷል። የክልሉ ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.