Logo
YenetaTube
የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ ከአሜሪካ እና እስራኤል በተሰነዘረ ጥቃት ከቤተሰቦቻቸው እና ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መገደላቸውን ባለሥልጣናት ማረጋገጣቸዉ ይታወቃል

የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ከሆነ ከበላይ መሪዉ በተጨማሪ፣ በዚሁ ጥቃት የአያቶላ አሊኻሜኒ ልጅ፣ አማች፣ የልጅ ልጅ እና ምራታቸውም ተገድለዋል።

በእስራኤል እና አሜሪካ ጥቃት የሞቱት የኢራን ባለስልጣናት ቁጥር ቢያንስ 40 እንደሚደርስም ተገልጿል።

ከተገደሉት ከፍተኛ አመራሮች መካከል ከፍተኛ አማካሪ እና የኒውክሌር ተደራዳሪ የሆኑት አሊ ሻምካኒ እንዲሁም የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል መሀመድ ፓክፑር እንደሚገኙበት ተዘግቧል።

ከአያቶላህ አሊ ጋር ስብሰባ ላይ የነበሩ 10 ከፍተኛ ባለልጣናት ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ማለፉ የተረጋገጠው አመራሮች የሚከተሉት ናቸው፦

አዚዝ ናሲርዛዴህ፦ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር።

ሌተናል ጄኔራል አብዱልራሂም ሞሳቪ፦ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ።

ሜጀር ጄኔራል መሀመድ ፓክፑር፦ የኢሊት እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) መሪ።

አሊ ሻምካኒ፦ የመከላከያ ም/ቤት ፀሐፊ።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት ምሽት በሰጡት መግለጫ "አብዛኛው የኢራን ከፍተኛ አመራር አልቋል" ማለታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የኢራኑ ታስኒም የዜና ወኪል ዛሬ ያወጣው መረጃ የትራምፕን ንግግር የሚያጠናክር ሆኗል።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.