ኢራን የመሪዋን አያቶላ አሊ ኻሜኒን ሞት አረጋገጠች
የኔታ ሚዲያ
የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ጥምር ጥቃት መገደላቸውን በይፋ አስታወቀ።
ዜናውን ያበሰረው ጋዜጠኛ ጥልቅ በሆነ ሐዘን እና በእንባ ታጅቦ በፋርሲ ቋንቋ ያነበበው ይፋዊ መግለጫ የሚከተለውን ይላል፦
"ያለ እረፍት እና ድካም ለዘለቀው የሁሴኒ ተጋድሎ ሕይወት በኋላ እንደ እስላማዊ ጥበቃ ጽኑ ተራራ በሆነው ታላቅ እና ሰማያዊ መንፈስ፤ የርኅራኄ እና የቁርጠኝነት አባት፣ የሙስሊሞች መሪ እና ኢማም፣ ክቡር አያቶላ ሰይድ አሊ ሁሴኒ ኻሜኒ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክን ቅዱስ መቅደስ ክብር የማስጠበቅ ጉዞ ላይ ሳሉ ጣፋጩን የሰማዕትነት ጽዋ በመጎንጨት ወደ ልዑል ሰማያዊው መንግሥት ተቀላቅለዋል።"
እንደ ዘገባው ከሆነ መሪው ለህልፈት የተዳረጉት በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የተሰነዘሩ ጥቃቶችን ተከትሎ ነው።
በቴህራን እና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ከፍተኛ የሐዘን ድባብ እየታየ ነው

3 months ago