Logo
FIDEL POST NEWS
❗️ፕሬዝዳንት ትራምፕ የአያቶላ አሊ ኻሜኒን መገደል አስታወቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውን በይፋ አስታወቁ።

ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያ ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ "በታሪክ ውስጥ እጅግ ክፉ ከሆኑ ሰዎች አንዱ የነበረው ኻሜኒ ሞቷል" ሲሉ ገልጸዋል።

​ግድያው የተፈጸመው አሜሪካ እና እስራኤል በጋራ ባደረጉት የተቀናጀ ጥቃት መሆኑን የገለጹት ትራምፕ፣ የቴክኖሎጂ የበላይነታቸውን በመጠቀም መሪውን መከታተል እንደቻሉ አብራርተዋል።

"ከእስራኤል ጋር በቅርበት በመስራት፣ እሱም ሆነ አብረውት የነበሩ ሌሎች መሪዎች ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም" ሲሉ አክለዋል።

​ይህ እርምጃ በኢራን እና በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣይ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ኢራን እስካሁን በመሪዋ ሞት ዙሪያ የሰጠችው ይፋዊ ምላሽ የለም።
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.