Logo
SeledaPost
በመካከለኛው ምስራቅ የቀሰቀሰው ጦርነት፤ የዱባይ የቅንጦት ሆቴል በኢራን ሚሳኤል ጋየ

​በዱባይ የሚገኘው ታዋቂው 'ፌርሞንት ዘ ፓልም' የቅንጦት ሆቴል በደረሰበት የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት አስተናገደ።

አደጋው የተከሰተው ኢራን በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላይ በሰነዘረችው የሚሳኤል ጥቃት ወቅት የተተኮሱ ሚሳኤሎች ተመተው ሲወድቁ ባረፉ ፍንጣሪዎች መሆኑ ተገልጿል።

​አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ "ኤፒክ ራዝ" እና "ላየንስ ሮር" የተሰኙ ጥቃቶችን መሰንዘራቸውን ተከትሎ፣ ኢራን በአጸፋው በዱባይ፣ ባህሬን እና ኳታር በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎች ላይ ጥቃት ፈጽማለች።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የመከላከያ ሚኒስቴር አዳዲስ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶችን ማክሸፉን አስታውቋል።

​በአሁኑ ወቅት በዱባይ አየር ማረፊያዎች ተዘግተው ከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ እየተደረገ ሲሆን፣ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ የት እንዳሉ አለመታወቁ በቀጠናው ያለውን ውጥረት ይበልጥ አባብሶታል።

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.