የማርኪንዮስ እና ክቫራትስኬሊያ ግቦች ሞናኮን ከሻምፒዮንስ ሊግ አሰናበቱ
በፓሪስ ፓርክ ደ ፕሪንስ ስታዲየም በተደረገው የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ፒኤስጂ እና ሞናኮ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ቢለያዩም፣ ፒኤስጂ በድምር ውጤት 5 ለ 4 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
ሞናኮ በ45ኛው ደቂቃ በአክሊውች ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም፣ በ58ኛው ደቂቃ ኩሊባሊ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ጨዋታውን ቀይሮታል።
ፒኤስጂዎች የተጫዋች ብልጫቸውን በመጠቀም በማርኪንዮስ እና በክቫራትስኬሊያ አማካኝነት ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ሞናኮ በጭማሪ ሰዓት የአቻነት ግብ ቢያስቆጥርም ፒኤስጂን ከውድድር ለማስወጣት ግን አልበቃውም።
በዚህም የፈረንሳዩ ሻምፒዮን ፒኤስጂ ከሪያል ማድሪድ እና ከአትላንታ ጋር በመሆን የ16ቱን ዙር መቀላቀሉን አረጋግጧል።

5 months ago