Logo
FastMereja
የ"ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የወጣቶች ውድድር በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

📌 አሸናፊዎች ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ይሳተፋሉ!
#fastmereja I ​ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 18 ለሆኑ ወጣቶች የተዘጋጀውና በዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ህብረት (ITU) የሚመራው "ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ" የወጣቶች ሀገራዊ ውድድር በይፋ መጀመሩ ተበሰረ።

በዘንድሮው ዓመት ተወዳዳሪዎች በምግብ ዋስትና እና በግብርና ላይ ለሚታዩ ችግሮች መፍትሔ የሚሆኑ ሮቦቶችን ይሠራሉ።

​ውድድሩ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

​በጁኒየር እና ሲኒየር ምድብ አሸናፊ የሚሆኑ ሁለት ቡድኖች በጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ሙሉ ወጪያቸው የተሸፈነ ጉዞ ይበረከትላቸዋል።

​ውድድሩ ወጣቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ (STEM) የታገዘ የችግር አፈታት ክህሎት እንዲያዳብሩና ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ መድረክ እንዲወክሉ ለማስቻል የታለመ ነው።

የውድድሩ አዘጋጅ የኤግዚት ሲስተምስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሰጡት መግለጫ፣ ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ መፍትሔ ፈጣሪ ለማድረግ የሚደረግ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳትሆን የመፍትሔ ፈጣሪ እንድትሆን እናስቀምጣት የተባለ ሲሆን በጋራ በመሆን 'ሮቦቲክስ ለበጎ ዓላማ' (Robotics for Good)ን ውድድር ብቻ ሳይሆን፣
ሀገራዊ ንቅናቄ እናደርገዋለን ብሏል።
#ኹነት

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.