Logo
FIDEL POST NEWS
የሆሊውድ ታላቁ ኮከብ እና ኦስካር ተሸላሚው ሮበርት ዱቫል በ95 ዓመቱ አረፈ

​በዓለም ሲኒማ ታሪክ ውስጥ ግዙፍ አሻራ ያሳረፈውና ለሰባት አስርት ዓመታት በስክሪን ላይ የቆየው አንጋፋው ተዋናይ ሮበርት ዱቫል (Robert Duvall) ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

​📌 ስለ ሮበርት ዱቫል የጥበብ ጉዞ፦
​የማይረሱ ስራዎቹ፦ በታዋቂው "The Godfather" ፊልም ላይ የቤተሰቡ አማካሪ (Tom Hagen) በመሆን እንዲሁም በ "Apocalypse Now" ፊልም ላይ ባሳየው ድንቅ ብቃትና ባደረገው የማይረሳ ንግግር ይታወቃል።

​የኦስካር ስኬት፦ ሰባት ጊዜ ለኦስካር ሽልማት የታጨ ሲሆን፣ በ1983 "Tender Mercies" በተሰኘው ፊልም ላይ ባሳየው ብቃት የ"ምርጥ ተዋናይ" (Best Actor) ሽልማትን አግኝቷል።

​ሁለገብ ጥበበኛ፦ ዱቫል ድንቅ ተዋናይ ብቻ ሳይሆን፣ ስኬታማ ዳይሬክተርና ፕሮድዩሰር ጭምር ነበር። "The Apostle" (1997) የተሰኘው ፊልሙን ራሱ ጽፎና ዳይሬክት አድርጎ ለኦስካር እጩ መሆን ችሏል።

​📌 የግል ህይወቱ እና ቤተሰቡ፦
​ትዳር፦ ሮበርት ዱቫል በህይወት ዘመኑ አራት ጊዜ ትዳር የመሰረተ ሲሆን፣ የመጨረሻዋና አሁን አብራው የነበረችው አርጀንቲናዊቷ ተዋናይት ሉሲያና ፔድራዛ ነች። የሚገርመው ሁለቱም የተወለዱት በአንድ ቀን (ጥር 5) ቢሆንም የ41 ዓመት የዕድሜ ልዩነት ነበራቸው።

​ልጆች፦ ሮበርት ዱቫል ምንም እንኳን የራሱ የሥጋ ልጆች ባይኖሩትም፣ ከመጀመሪያ ሚስቱ ጋር በነበረው ቆይታ የሁለት የእንጀራ ልጆቹ (Step-daughters) አባት ሆኖ አሳድጓል።

​የህልፈቱ ዜና በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ የጥበብ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ሀዘንን ፈጥሯል።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.