የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን የሮይተርስ ጋዜጠኞችን እውቅና ሰረዘ
የኢትዮጵያ ሚዲያ ባለስልጣን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ባደረጉ ሶስት የሮይተርስ (Reuters) ጋዜጠኞች ላይ የሰጠውን የጋዜጠኝነት እውቅና (Accreditation) ማደስ አለመፈለጉን የዜና ወኪሉ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከእውቅና እገዳው በተጨማሪ የካቲት 7 እና 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን 39ኛውን የኤፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ለመዘገብ ለተቋሙ ተሰጥቶ የነበረውን ልዩ የፈቃድ ወረቀት መሰረዙ ተገልጿል።
ምንም እንኳን የሚዲያ ባለስልጣኑ እስካሁን በይፋ የሰጠው መግለጫ ባይኖርም ውሳኔው የተላለፈው የዜና ወኪሉ ከጥቂት ቀናት በፊት (የካቲት 3 ቀን) ካወጣው የምርመራ ዘገባ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ተጠቁሟል።
ሮይተርስ በዘገባው ኢትዮጵያ በጎረቤት ሱዳን ከሚገኘው የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይል (RSF) ጋር ግንኙነት ላላቸው ታጣቂዎች ሚስጥራዊ የልምምድ ጣቢያ አዘጋጅታለች የሚል ክስ አቅርቦ ነበር።
የኢትዮጵያ መንግስት ግን በሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደሌለውና ስለተባለውም ጣቢያ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ቀደም ብሎ ማስተባበሉ ይታወሳል።
የዜና ወኪሉ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ "ሮይተርስ የተፈጠረውን ሁኔታ እየገመገመ ይገኛል ሆኖም 'የቶምሰን ሮይተርስ የጥቅም መርሆዎችን' (Trust Principles) ባከበረ መልኩ ገለልተኛ ሚዛናዊና ተአማኒነት ያለው ዘገባ ስለ ኢትዮጵያ ማቅረቡን ይቀጥላል" ብሏል።
ይህ የእውቅና ስረዛ የተካሄደው በርካታ የአፍሪካ መሪዎችና ዲፕሎማቶች ለህብረቱ ጉባኤ አዲስ አበባ በሚገኙበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ትኩረት የሚስብ አድርጎታል።

6 months ago