Logo
Getu Temesgen
🌍 "የህዳሴው ግድብ (GERD) ለአፍሪካ የራስ አቅም ግንባታ ተምሳሌት ነው!"

- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን 🇪🇹💡

​#ethiopia | አፍሪካ ያላትን 4.6 ትሪሊዮን ዶላር ሀብት በመጠቀም የራሷን ፕሮጀክቶች መገንባት እንደምትችል ግድቡ አሳይቷል

​የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ መቃረቡን ተከትሎ፤ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም እና በሀገር ውስጥ ሀብት (Domestic Resources) ግዙፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት እንደሚችሉ ያሳየ "ሕያው ተምሳሌት" (Model) አድርጎ አቅርቦታል።

​የኮሚሽኑ መልዕክት:

አሁን ላይ 300 ሚሊዮን አፍሪካውያን የንጹህ ውሃ አቅርቦት ችግር ያለባቸው ሲሆን፤ ይህንን ለመፍታት የ30 ቢሊዮን ዶላር ክፍተት አለ። ኮሚሽኑ አገራት ይህንን ክፍተት ለመሙላት የውጭ እርዳታን ከመጠበቅ ይልቅ፤ ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ እንዳደረገችው የአፍሪካን 4.6 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት የተፈጥሮ እና የገንዘብ ሀብት (Assets) ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው አሳስቧል።

​ይህም የአፍሪካን የልማት ፕሮግራም (PIDA) ለማፋጠን እና የአጀንዳ 2063 ራዕይን ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ ነው።

​የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ኩራት ነው!

​#gerd #africanunion #ausummit #agenda2063 #infrastructure #ethiopia #africarising #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.