Logo
FIDEL POST NEWS
ብሪትኒ ስፒርስ የሙዚቃ ንብረቶቿን በ200 ሚሊዮን ዶላር ሸጠች!

​የፖፕ ሙዚቃ ንግሥቷ ብሪትኒ ስፒርስ በሙዚቃ ታሪኳ ትልቅ የተባለውን ውሳኔ አሳለፈች። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ ድምፃዊቷ ከፈረንጆቹ 1999 ጀምሮ የነበሯትን የሙዚቃ ሥራዎቿን በሙሉ (Music Catalog) ለPrimary Wave ኩባንያ በ200 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አድርጋለች።

​📌 የውሳኔው ዝርዝር ነጥቦች፡
​ሽያጩ፡ ከታዋቂው "...Baby One More Time" ጀምሮ እስከ መጨረሻዎቹ የሙዚቃ ሥራዎቿ ያሉትን መብቶች ያካትታል።

​ቃሏን ጠብቃለች፡ የ44 ዓመቷ ብሪትኒ ከዚህ ቀደም "ወደ ሙዚቃው ኢንዱስትሪ ዳግም አልመለስም" ስትል የገባችውን ቃል ተግባራዊ ማድረጓ ተገልጿል።

​ከባድ ውሳኔ፡ ይህ ሽያጭ ለብሪትኒ የገንዘብ ምንጭ ብቻ ሳይሆን፣ ላለፉት ዓመታት ከነበረባት የአባቷ ጥብቅ ቁጥጥር (Conservatorship) እና ካለፈው የጭንቀት ሕይወቷ ሙሉ በሙሉ የመውጫ መንገድ እንደሆነላት ታምኖበታል።

​💰 ወደ ቢሊየነሮች መንደር፡
በዚህ ውሳኔዋ እንደ ብሩስ ስፕሪንግስተን እና ጀስቲን ቢበር ያሉ ዝነኞችን ተቀላቅላለች። እነሱም በተመሳሳይ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠር ዶላር መሸጣቸው ይታወሳል።

​📖 አዲስ ሕይወት፡
"The Woman in Me" በሚለው መጽሐፏ የሕይወቷን ምስጢር ይፋ ካደረገች በኋላ፣ አሁን ደግሞ የሙዚቃ ሀብቷን በመሸጥ ከካሜራና ከታዋቂነት ርቃ ሰላማዊ ሕይወት ለመኖር መምረጧን የቅርብ ምንጮች ይናገራሉ።
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.