መንግሥት ተጨማሪ ታክሶችን ሊጥል ነው ተባለ።
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ከደረጋቸው ለውጦች አንዱና በተፅዕኖው የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የሚነካው የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ነው።
የአለም የገንዘብ ድርጅትን ቅድመ ሁኔታዎች የተከተለውንና መንግስት “ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ” ሲል የጠራው ፕሮግራም በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2019 ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም በትግራዩ ጦርነት ሳቢያ ተጓትቶ የሁለተኛውና “የተሟላ” ነው የተባለው መርሀ ግብር በ2024 (ሐምሌ 2016) ተጀምሯል።
ይህን ማሻሻያ በተመለከተ የአይኤምኤፍ (IMF) ከሰሞኑ በሂደቱ ላይ ጥልቅ ግምገማ አድርጓል።
ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር በዝግ ባደረገው ውይይት የተነሱ ፍሬ ሐሳቦች፤ የተወሰዱ እርምጃዎችና ወደፊት የተያዙ ዕቅዶች ተዘርዝረዋል።
ዋዜማ ራድዮ ተመለከትኩት ባለው የIMF ሪፖርት መሰረት መንግሥት አዳዲስ ታክሶችን ለመጣል ተዘጋጅቷል።
የገንዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ ለIMF ዋና ዳይሬክተር ባለፈው ወር የጻፉት ደብዳቤም በዚህ የIMF ሰነድ ውስጥ ተካቷል፡፡
ደብዳቤው እንደሚለው መንግሥት ብዙ ዓይነት ታክሶችን ለመጣል እያሰበ ነው፡፡
ከእነዚህም አንዱ የተሽከርካሪ ባለቤትነት ግብር ሪፎርም ነው፤ ክልሎችና ፌደራል መንግስት ይሄን ግብር በሚሰበስቡበት ሁኔታ ላይ በቅርቡ በፓርላማ ምክክር እንደሚደረግም ሰነዱ ይገልጻል፡፡
የመንግሥት ገቢ ማሰባሰብን በተመለከተ IMF ባዘዘው መሠረት፤ መንግሥት በነዳጅ፣ ኤሌክትሪክ፣ ቴሌ፣ ማዳበሪያና ሌሎች የሚያደርገውን ድጐማ በማንሳት የመንግሥት ገቢን ሲያሳብጥ የሕዝቡን ኑሮ እያጎሳቆለ ይገኛል፡፡
seledadotio

6 months ago