Logo
FIDEL POST NEWS
በኢራን የተለያዩ ከተሞች ፍንዳታዎች ተከሰቱ

​በዛሬው ለሊት በኢራን የተለያዩ ከተሞች በተከሰቱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 6 ሰዎች መሞታቸውን እና በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

​አህቫዝ : በከተማዋ በሚገኝ የመኖሪያ መንደር ውስጥ በደረሰ የጋዝ ፍንዳታ 4 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል።

​ባንደር አባስ (: ስትራቴጂካዊ በሆነችው በዚህች የወደብ ከተማ ባለ 8 ፎቅ ሕንፃ ላይ በደረሰ ፍንዳታ የአንዲት የ4 ዓመት ህፃን ሕይወት ሲያልፍ፣ 14 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

​የፍንዳታው መንስኤ: የከተማዋ የእሳት አደጋ መከላከያ ፍንዳታው በጋዝ መፍሰስ (Gas Leak) ሳቢያ መከሰቱን ቢገልጽም፣ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው።

​ወታደራዊ ጥርጣሬ: ፍንዳታው የተከሰተው ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ (Strait of Hormuz) ላይ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት በመሆኑ ስጋት ፈጥሯል።

ሆኖም የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባህር ኃይል አዛዥ አሊሬዛ ታንግሲሪ ላይ የግድያ ሙከራ ተደርጓል የሚባለውን ወሬ አስተባብሏል።

​እስራኤል: የእስራኤል ባለስልጣናት በበኩላቸው በነዚህ ፍንዳታዎች ላይ ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንደሌላቸው ለሮይተርስ ገልጸዋል።

​ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል ያለው ውጥረት በከረረበት እና በሀገሪቱ ውስጥ የሕዝብ ተቃውሞዎች ባሉበት ወቅት ነው።
4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.