⚽️ አሰልጣኙ ብሆንም ደግሞም አባቱም ነኝ
#ethiopia | የቀድሞው የዓለም ኮከብ እና የአሁኑ የፌይኖርድ ዋና አሰልጣኝ ሮቢን ቫን ፐርሲ፣ ትላንት ምሽት በሜዳ ላይ ያሳየው ስሜታዊ ድርጊት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል። በጨዋታው ወቅት ልጁ ሻኩዌል ቫን ፐርሲ ላይ ከባድ የጉልበት ጉዳት ማጋጠሙን ተከትሎ፣ ቫን ፐርሲ የአሰልጣኝነት ሚናውን ለጥቂት ደቂቃዎች ወደ ጎን በመተው አባትነቱን አስቀድሟል።
💔 በሜዳ ላይ የተከሰተው ክስተት
ወጣቱ ሻኩዌል ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ሲወጣ፣ አሰልጣኝ ቫን ፐርሲ በጭንቀት ተውጦ ወደ ህክምና ባለሙያዎቹ ጋር በማምራት ልጁን አቅፎ ሲያጽናናው ታይቷል። ይህ ቅጽበት በስፖርቱ ዓለም "ከውጤት በላይ የሰው ልጅነት ይበልጣል" የሚል መልዕክት ያስተላለፈ ነበር።
💬 "አሰልጣኝ ብሆንም፣ ከሁሉም በላይ አባቱ ነኝ"
ከጨዋታው በኋላ በሰጠው መግለጫ ቫን ፐርሲ ስሜቱን እንዲህ ገልጿል፦
"አዎ፣ እኔ የአሰልጣኝነት ሃላፊነት አለብኝ፤ ነገር ግን ከምንም ነገር በላይ እኔ የሻኩዌል አባት ነኝ። እንደዚህ አይነት ጉዳት ሲያጋጥም ለማንኛውም ተጫዋች ትጨነቃለህ፣ ለገዛ ልጅህ ሲሆን ደግሞ ስሜቱ ይበረታል።"
አሰልጣኙ አክሎም የጉዳቱ ሁኔታ ስጋት የሚጭር መሆኑን ጠቁሟል፦ "ጉዳቱ ከባድ እንዳይሆን ተስፋ እናደርጋለን፤ ሆኖም ምልክቶቹን ስታይ ጥሩ አይመስሉም። በጣም ያማል።"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #robinvanpersie #shaqueelvanpersie #feyenoord #footballfamily #injuryupdate #fatherandson #eredivisie

4 months ago