Logo
FIDEL POST NEWS
ጦርነት ወይስ ዝግጅት? አሜሪካ ግዙፍ የጦር አውሮፕላኖቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያጋዘች ነው

​አሜሪካ በታሪኳ ከፍተኛ ተባለ የተባለለትን የአየር ኃይል ስምሪት በመካከለኛው ምስራቅ እያደረገች መሆኑ ተሰማ።

ይህ እርምጃ በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የታሰበ ይሆን? የሚለው ጥያቄ በአለም አቀፍ ተንታኞች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።

​ባለፉት 24 ሰዓታት የታዩ ወሳኝ እንቅስቃሴዎች፦

​የነዳጅ ጫኝ እና የትራንስፖርት አውሮፕላኖች፦ በርካታ KC-46A የነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች እና ቢያንስ 9 C-17 ግዙፍ የትራንስፖርት አውሮፕላኖች ከቴክሳስ ፎርት ሁድ ተነስተው ወደ ቀጠናው ገብተዋል።

​የሚሳኤል መከላከያ ዘዴዎች፦ አውሮፕላኖቹ የአሜሪካን የጦር ሰፈሮች እና እስራኤልን ሊሰነዘር ከሚችል ጥቃት ለመከላከል የሚያገለግሉ የረቀቁ የፀረ-አውሮፕላን መከላከያ ዘዴዎችን እንደጫኑ ተገልጿል።

​የአየር ላይ እዝ ፦ ሁሉንም የግንኙነት መረቦች ለማቀናጀትና ውስብስብ ወታደራዊ ዘመቻዎችን ለመምራት የሚያገለግል ልዩ አውሮፕላን በኳታር አል ኡደይድ የጦር ሰፈር አርፏል።

​የተዋጊ ጄቶች ክምችት፦ ቀደም ብለው ከደረሱት F-15፣ F-16፣ F-22 Raptor እና F-35 ተዋጊ ጄቶች ጋር ተደምሮ፣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው የአሜሪካ አየር ኃይል በቅርብ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ግዙፍ ስብስብ ሆኗል።

​ለምን አሁን?

ይህ እንቅስቃሴ በኢራን ውስጥ ካለው የህዝብ ተቃውሞ እና ተያያዥ ውጥረቶች ጋር የሚገጣጠም ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ እንቅስቃሴውን "ታላቁ የጦር መርከቦች ስብስብ (Massive Armada)" ሲሉ ጠርተውታል። አሜሪካ "ለማንኛውም ጥቃት ዝግጁ ነን" ስትል፣ ኢራን በበኩሏ "ጥቃት ቢሰነዘርብን ጦርነቱ ሁሉን አቀፍ ይሆናል" የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።
6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.