በኢትዮጵያ የወርቅ ልማት ላይ የተሰማራው አላይድ ጎልድ በቻይናው ዚጂን ሊጠቅለል ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ፣ በማሊ እና በኮትዲቩዋር ግዙፍ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክቶች ያሉት ካናዳዊው አላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን ፣ በሆንግ ኮንግ የአክሲዮን ገበያ ከተመዘገበው ዚጂን ጎልድ ኢንተርናሽናል ኩባንያ ጋር የመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ።
በዚህም መሠረት ዚጂን ጎልድ ሁሉንም የአላይድ ጎልድ አክሲዮኖች በአንድ አክሲዮን 44 የካናዳ ዶላር በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ለመግዛት ተስማምቷል።
ይህም ኩባንያው ባለፉት 30 ቀናት በገበያ ላይ ከነበረው አማካይ ዋጋ የ27% ብልጫ ያለው በመሆኑ ለባለአክሲዮኖች ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኝና ፈጣን የገንዘብ ክፍያ የሚያረጋግጥ መሆኑ ተገልጿል።
በቶሮንቶ ካናዳ ይፋ የተደረገው ይህ በሁለቱ ኩባንያዎች መካከል የተደረገው የወዳጅነት የሽያጭ ስምምነት 5.5 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር (C$5.5 Billion) ዋጋ የተሰጠው ሲሆን፣ ክፍያውም ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ የሚፈጸም መሆኑ ተገልጿል።
የዚጂን ጎልድ ሊቀመንበር ሆንግፉ ሊን እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው የኩርሙክ ፕሮጀክት እና በማሊ የሚገኘው ሳዲዮላ "የትውልድ ሀብቶች" መሆናቸውን ጠቅሰው፣ አዲሱ ባለቤት እነዚህን ፕሮጀክቶች ለበርካታ አስርት ዓመታት ምርት እንዲሰጡ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የአላይድ ጎልድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ማሮን በበኩላቸው፣ ይህ ሽያጭ ቡድናቸው በአፍሪካ ያለውን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ሀብት ለማልማት ላደረገው ጥረት ትልቅ እውቅና መሆኑን ገልጸው፣ ዚጂን ጎልድ በዓለም ካሉ ግዙፍ የማዕድን ኩባንያዎች አንዱ በመሆኑ የጀመሩትን ፕሮጀክት ዳር ለማድረስ አቅም እንዳለው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሊቀመንበር ሆንግፉ ሊንም በበኩላቸው በኢትዮጵያ፣ በማሊ እና በኮትዲቩዋር ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚጓጉና ግዥው በአፍሪካ ያለባቸውን ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው አብራርተዋል።
ይህ ግዙፍ ግዥ በጥሬ ገንዘብ የሚፈጸም በመሆኑና ዚጂን ጎልድ ክፍያውን በእጁ ላይ ካለው ተቀማጭ የሚሸፍን በመሆኑ፣ በብድር ምክንያት የሚፈጠር ምንም ዓይነት መዘግየት እንደማይኖር ተገልጿል።
የአላይድ ጎልድ የዳይሬክተሮች ቦርድም ባለአክሲዮኖች ለዚህ ስምምነት ድጋፋቸውን እንዲሰጡ በሙሉ ድምጽ መክሯል። ግዥው በካናዳ ፍርድ ቤት፣ በባለአክሲዮኖች እና በቻይና መንግስት የቁጥጥር ተቋማት ተቀባይነት አግኝቶ እስከ መጪው ሚያዝያ 2026 ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ስምምነቱ ሲጠናቀቅ አላይድ ጎልድ ከቶሮንቶ እና ከኒውዮርክ የአክሲዮን ገበያዎች እንደሚሰረዝ ታውቋል።
#ቅዳሜገበያ #etbusinessview #ethiopia #zijin #allied Gold
#china #canada

6 months ago