Logo
FastMereja
በጉራጌ ሀገረ ስብክት የምትገኘው ቆጠር ገድራ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር ተዘጋጀ!

በጉራጌ ሀገረ ስብክት የምትገኘው ቆጠር ገድራ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስትያን በበጎ አባቶች እና በምዕመናን እነሳሽነት እየታነፀች ትገኛለች የተጀመረውን ሕንፃ ቤተክርስቲያን ለማስፈጸም ከጥር 29 እስከ የካቲት 01/2018 ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የቀጥታ ሥርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

የቀጥታ ስርጭት መርሀ-ግብሩ በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

ይህ ቤተ ክርስቲያን በዕድሜ ብዛት በመጎዳቱ በየጊዜው ዕድሳት እየተደረገለት እስከዛሬ መቆየቱ ተገልፆ በአሁኑ ሰዓትም ለበርካታ ሕዝበ ክርስቲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ቆጠር, የሚለው ቃል ቦታውን የመሠረቱት ግለሰብ ስም ሲኾን፣ በጊዜ ሒደት ቃሉ የጎሣ መጠርያ ኾኖ ቀጥሏል። ገድራ, በአካባቢው ቋንቋ የዛፍ ዓይነትን የሚያመለክት ቃል ነው።

በቆጠር ገድራ በአንድ ወቅት በተደረገ ቁፋሮ ሰባት ጥንታውያን የዋሻ ቤተ መቅደሶች፣ ሦስት የሱባዔ መያዣ ቦታዎችና ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳት ተገኝተዋል፡፡

ይህም በዚያ ሥፍራ ቀደም ሲል ቤተ ክርስቲያን ታንጾ እንደ ነበር የሚጠቁም ማስረጃ መሆኑ እና በቁፋሮ የተገኙ ሰባቱ የዋሻ ቤተ መቅደሶችም:- የደብረ ቢዘን ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጎልጎታ፣ ቤተ መድኅን፣ ቤተ ጠበብት፣ ቤተ ኤፍራታ፣ ቤተ ደብረ ብርሃን እና ቤተ ደናግል ይባላሉ።

ከእነዚህ ቤተ መቅደሶች መካከል በቤተ ጎልጎታ የኦሪት መሥዋዕት ይቀርብበት እንደ ነበረ፤ በውስጡም ከወርቅ የተሠራ መሠዊያ እንደ ተገኘና ይህን መሠዊያም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሥፍራው ሲያገለግሉ የነበሩ አባ ማትያስ የተባሉ አባት እንዳይዘረፍ ብለው ቆፈረው እንደ ቀበሩት የአካባቢውን ታሪክ የሚያውቁ አባቶች ይናገራሉ፡፡

በመሆኑም በበኩረ ምእመናን ቀኝ አዝማች ትዕዛዙ ኮሬ ሰብሳቢነት፣ በአካባቢው ተወላጆች፣ በደጋግ የጉራጌ ማኅበረሰብ እና በመላው ዓለም በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የኪዳነ ምሕረት ወዳጆች የተጀመረው ይህ ገዳሙን የማሳደግ ሥራ ዓላማው በየጊዜው እየቀዘቀዘ የመጣውን የአብነት ትምህርት ለማስፋፋት፣ ጥንታውያን ቅርሶችን በመጠበቅ ለትውልድ ለማስተላለፍ፣ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማሳደግ፣ ስብከተ ወንጌልን በስፋት ለማዳረስ በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰአት በተዘጋጀዉ ቀጥታ ስርጭት ሁላችሁም በመገኘት የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ስልክ
0911512707
0913380901
0911751529
ባንክ አካውንት፦1000257570103 ቆጠር ገድራ መካነ ቅዱሳን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.