Logo
FIDEL POST NEWS
የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኢ ታካኢቺ ፓርላማውን በተኑ

​የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኢ ታካኢቺ የሀገሪቱን የታችኛው ምክር ቤት (House of Representatives) በዛሬው ዕለት በይፋ መበተናቸውን አስታወቁ።

​ምክንያት፦ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ፓርላማውን የበተኑት አዲስ የህዝብ ውክልና (Mandate) ለማግኘትና የጀመሩትን የኢኮኖሚና የደህንነት ፖሊሲ ለማስፈጸም እንዲረዳቸው ነው።

​የምርጫ ቀን፦ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫው በፈረንጆቹ የካቲት 8 ቀን 2026 እንዲካሄድ ተወስኗል።

​ታሪካዊ ክስተት፦ ታካኢቺ ባለፈው ጥቅምት ወር ስልጣን የያዙ ሲሆን፣ የጃፓን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ይታወሳል። ፓርላማው በመደበኛ ስብሰባው መጀመሪያ ላይ እንዲበተን መደረጉ ላለፉት 60 ዓመታት ያልታየ ክስተት መሆኑ ተገልጿል።

​የተቃውሞ ድምፆች፦ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውሳኔውን የተቹ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሯ የ2026 በጀት ከመፅደቁ በፊት ምርጫ መጥራታቸው ለሀገር አስተዳደር ሳይሆን ለፖለቲካ ጥቅማቸው ቅድሚያ ሰጥተዋል በሚል እየወቀሱ ይገኛሉ።

​ምርጫው ታካኢቺ ከጃፓን ኢኖቬሽን ፓርቲ (Japan Innovation Party) ጋር የመሰረቱት ጥምረት ምን ያህል የህዝብ ድጋፍ እንዳለው የሚፈተሽበት ትልቅ መድረክ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.