Logo
FastMereja
6ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር፣ ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ ከጥር 19 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው!!

በሀገራችን የፈርኒቸር ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ዘርፍ ትልቅ ድርሻ ያለው “6ኛው ፊንቴክስ የፈርኒቸር፣ ቤተ- ውበትና የግንባታ አጨራረስ ኤክስፖ” ከጥር 19 እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለ 4 ተከታታይ ቀናት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታወቁ።

ይህ ታላቅ ኤክስፖ በዋናነት በፈርኒቸር አምራቾች፣ በቤተ-ውበት እና በግንባታ አጨራረስ ስራ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሰፊ የገበያ አማራጭ ይዞ መቅረቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በርካታ አምራቾች እና አስመጪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በኤክስፖው ላይ የሚሳተፉ ዋና ዋና ዘርፎች፦
• የፈርኒቸር (Furniture) እና የቤተ ውበት (Interior design) ውጤቶች፣
• የሴራሚክስ (Ceramics)፣ የወለል ንጣፎች (Flooring) እና የጣራ ክዳን (Roofing) ምርቶች፣
• ቀለሞች (Paint) እና ዘመናዊ የመብራት (Lighting) ስርዓቶች፣
• የመታጠቢያ ቤት ማጠናቀቂያዎች (Bathroom finishing materials) ፣
• የስፖንጅና የፍራሽ (Foam & Mattress) ምርቶች እና ሌሎችም የግንባታ ማጠናቀቂያ ግብዓቶች በስፋት ለእይታ ይቀርባሉ።

እንደ አዘጋጆቹ ገለጻ፣ ኤክስፖው የመንግስት የግዢ ቢሮዎች፣ አርክቴክቶች፣ ስራ ተቋራጮች፣ የሪል ስቴት አልሚዎች እንዲሁም የሆቴል እና የትምህርት ቤት ግንቢዎች ከአምራቾች ጋር ቀጥተኛ የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ይህንን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ኤክስፖ እንደተለመደው ፕራና ኢቨንትስ (Prana Events) ከአፍሪካ ትረስትድ ፓርትነርስ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፣ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ግለሰብ በነፃ መጎብኘት እንደሚችል ታውቋል።

ተጨማሪ መረጃ፡ ኤክስፖውን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ሁሉ በድረ-ገጽ https://pranaevents.net/fi... ቀድመው እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል።

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.