Logo
Getu Temesgen
🔴 አርሰናል ወርቃማ እድል አበላሸ! 😫

​"መድፈኞቹ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ነጥብ ጣሉ"
#ethiopia | ​የሊጉ መሪ አርሰናል በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት በመለያየት ነጥብ ጥሏል።

​ለምን ወርቃማ እድል ተባለ?
ተቀዳሚ ተፎካካሪው ማንችስተር ሲቲ በዩናይትድ መሸነፉን ተከትሎ፤ አርሰናል ይህንን ጨዋታ ቢያሸንፍ ኖሮ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 9 (ዘጠኝ) በማስፋት የዋንጫ ጉዞውን ማመቻቸት ይችል ነበር። ሆኖም ይህንን እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

​የአርሰናል ወቅታዊ ቁጥሮች፡-
​ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል አቻ ከተለያየ በኋላ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ተከታታይ ነጥብ የጣለበት ነው።

​በውድድር ዓመቱ ለ5ኛ ጊዜ አቻ ወጥቷል።

​አሁን ላይ በ50 ነጥብ ሊጉን እየመራ ሲሆን፤ ከ2ኛው ማንችስተር ሲቲ በ 7 ነጥብ ርቆ ይገኛል።

​#arsenal #nottinghamforest #pl #coyg #miklarteta #premierleague #ethiopia

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.