Logo
FastMereja
ቺቫን ፕሮፐርቲስ ቅንጡ አፓርትመንት አስመረቀ!
#fastmereja :- በሀገራችን የግንባታ ዘርፍ ለ17 ዓመታት ስኬታማ ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው ቺባን ፕሮፐርቲስ፣ "ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" የተሰኘ የባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ደረጃና አገልግሎት የሚሰጥ ቅንጡ (Luxury) አፓርትመንት በዛሬዉ እለት አስመርቋል።

ይህ አዲስ አፓርትመንት በሀገሪቱ የሪል ስቴት ልማት ዘርፍ አዲስ የአኗኗር ዘይቤን ለማስተዋወቅ ታቅዶ የተገነባ እንደሆነም ተገልጿል።

"ቺባን አልፋ ሬዚደንስ" ነዋሪዎች የቅንጡ ሆቴል አገልግሎትን በቤታቸው እንዲያገኙ በሚያስችል መልኩ
ሰፊ የሆቴል ሎቢ፣ ሬስቶራንት፣ ካፌ፣ የጂም ማዕከል እና በሀገራችን የመጀመሪያው የሆነ ትልቅ "ኢንፊኒቲ ፑል" (Infinity Pool) በህንጻው አናት ላይ ተገንብቶለታል።

የቤት አማራጮቹ ከስቱዲዮ እስከ ባለ ሦስት መኝታ ክፍሎች ያሉት ሲሆን፣ በህንጻው አናት ላይ ባለ ሁለት ወለል ግዙፍና ቅንጡ ፔንት ሀውሶችን (Pent-houses) ይዟል።

ለስምንት ዓመታት ያህል የገበያ ጥናትና ዝግጅት ሲደረግበት የቆየው ይህ ፕሮጀክት፣ አሁን ላይ የግንባታው ሂደት ለነዋሪዎች ምቹ ወደሆነ ደረጃ መድረሱ ተገልጿል።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.