ሶማሊላንድ በበርበራ ወደብ ላይ በሶማሊያ የሚነሳባትን የይገባኛል ጥያቄ “መሠረተ ቢስ” ስትል አጣጣለች
የሶማሊላንድ መንግሥት የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግሥት በበርበራ ወደብ ላይ የሚያነሳውን ማንኛውንም ዓይነት የይገባኛል ጥያቄ “መሠረተ ቢስና ሕጋዊ ተቀባይነት የሌለው” ሲል ተቃወመ።
የሞቃዲሾ መንግሥት በሶማሊላንድ ግዛትም ሆነ በምታደርጋቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ላይ ምንም ዓይነት አስተዳደራዊ ስልጣን፣ ሕጋዊ ውክልና ወይም ቁመና እንደሌለው መግለጫው አመልክቷል።
ሶማሊላንድ ይህንን ምላሽ የሰጠችው ሶማሊያ የበርበራ ወደብን በሚመለከት ለምታወጣቸው ተደጋጋሚ መግለጫዎች ነው።
በመግለጫው በሶማሊላንድ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል የተደረጉት የበርበራ ወደብ ልማት ስምምነቶች በሙሉ ሕጋዊና አስገዳጅ መሆናቸው ተገልጿል።
እነዚህ ስምምነቶች በሶማሊያ ተቃውሞ የማይታገዱ ወይም የማይቀየሩ ናቸው ስትል
ሶማሊላንድ ገልፃለች።
ሶማሊላንድ በራሷ ግዛት ውስጥ የኢኮኖሚ አጋርነቶችን የመፍጠርና የማስተዳደር ሙሉ መብቷን ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ትጠቀማለች ስትል ገልፃለች።

7 months ago