Logo
FastMereja
በኢትዮጵያ በካንሰር ከሚጠቁ ሕፃናት መካከል የሚያገግሙት ከ30% በታች መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ በየዓመቱ በካንሰር ከሚጠቁ ከ6,000 በላይ ሕፃናት መካከል ሕክምና የሚያገኙት ከ2,000 የማይበልጡት ብቻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የሕፃናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር (ESPHO) አስታወቀ።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አቤል ሀይሉ እንደገለጹት፣ አብዛኞቹ ሕፃናት ወደ ሕክምና የሚመጡት በሽታው በሦስተኛና በአራተኛ ደረጃ ላይ ደርሶ በመሆኑ የማገገም ዕድላቸው ከ30 በመቶ በታች ዝቅ እንዲል አድርጎታል። ይህንን አሳሳቢ ችግር ለመፍታትም ስፔሻሊስቶችንና ባለድርሻ አካላትን ያሰባሰበው የኢትዮጵያ የሕፃናት የደምና ካንሰር ሕክምና ማኅበር (ESPHO) ዛሬ በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

ማኅበሩ በቀጣይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር፦
• የማኅበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሕፃናት በጊዜ ሕክምና እንዲያገኙ ማድረግ፣
• ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ጥናታዊ መረጃዎችን ማቅረብ ላይ ትኩረት አድርጎ ይሠራል ተብሏል።

በምስረታው ወቅት ከ10 በላይ ዓለም አቀፍ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተው የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.